ሽመልስ በቀለ ግብ አስቆጠረ

ለግብፁ ፔትሮጀት ክለብ በመጫወት ላይ የሚገኘው ኢትዮጵዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ ትላንት ማምሻውን በተደረገ የግብፅ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ አሶዮቲ ስፖርት ላይ ግብ አስቆጥሯል፡፡ ፔትሮ ጀት ጨዋታውን 3ለ2 አሸንፎ የወጣ ሲሆን ሽመልስ ግቧን በ61ኛው ደቂቃ ነበር ማስቆጠር የቻለው፡፡ እስካሁን ያስቆጠረውን የግብ መጠንም 6 አድርሷል፡፡

በተያየዘ ዜና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል እና የፊት መስመር ተሰላፊ የሆነው ሳላዲን ሰዒድ ለክለቡ በተጠባባቂ ወንበር ባሳለፈበት ጨዋታ አልአህሊ ከ ኢስማኤሊ ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ከጉዳት መልስ ሳላዲን ቋሚ ሆኖ ለመሰለፍ እየተሳነው ነው፡፡ የግብፅ ፕሪምርሊግን ዛማሌክ በ48 ነጥብ ሲመራ ፣ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ እና አል አህሊ በ43 እና በ39 ነጥብ 2ተኛ እና 3ተኛ ናቸው፡፡ የሽመልሱ ፔትሮጄት በ30 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሽመልስ በቀለ ግብ ይህንን ይመስላል፡-

http://www.youtube.com/watch?v=sRJ6dcgncgo

ያጋሩ