መድን ከካሜሩን ተጫዋች አስፈረመ

በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ የመጨረሻ ደረጃን ይዞ አንደኛውን ዙር ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን ከሊጉ ላለመውረድ በዝውውር መስኮቱ ቡድኑን በተጫዋቾች ማጠናከሩን ቀጥሎበታል፡፡ የአስራት ኃይሌው ቡድን ከሃገር ውስጥ ዝውውሮች በተጨማሪ ወደ ምእራብ አፍሪካም በማቅናት ተጫዋች ማስፈረማቸውን ሳምንታዊው ሀት-ትሪክ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ኡኩድ የተባለው ይኸው ተጫዋች ካሜሩናዊ ዜግነት ያለው ሲሆን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ነው፡፡ መድን ለዝውውሩ ምንም ክፍያ ያልፈፀመ ሲሆን የክለቡን ከፍተኛ ደሞዝ ለመክፈል ከተጫዋቹ እንደ ተስማማ ተናግሯል፡፡ በእድሜ እና ጉዳት የሳሳው የመድን የአማካይ ክፍልን ለማጠንከር አሰልጣኝ አስራት በርካታ ተጫዋቾች ለማስፈረም እየጣሩ ሲሆን የካሜሩናዊው መምጣት በአማካይ ክፍሉ ላይ አዲስ ሃይል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መድን በዝውውር መስኮቱ እስካሁን ካሜሩናዊውን ጨምሮ መሃመድ ናስርን ከአህሊ-ሼንዲ በ300 ሺህ ብር ፣ ፉአድ ቃዲን ከአዳማ ከነማ በውሰት አዘዋውረዋል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ