“የምድቡ ከባድ ተፎካካሪያችን ኢትዮጵያ ነች፡፡ ” ክርስቲያን ጎርከፍ

ጋቦን ለምታዘጋጀው ለ31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 10 ከኢትዮጵያ ፣ ሌሴቶ እና ሲሸልስ ጋር የተደለደለው የአልጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ክርስቲያን ጎርከፍ በማጣሪያው ኢትዮጵያ በንፅፅር አልጄሪያን እንደምትፈትን ገልፀዋል፡፡ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የተሻለ ዕድል ይዛለች፡፡ ጎርከፍ የ1990 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ አልጄሪ㝕 ከባድ ተፎካካሪ ልትሆን የምትችለው ኢትዮጵያ እንደምትሆን እምነታቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

“የማጣሪያ ጨዋታዎቹ ቀላል አይሆኑም፡፡ ሲሸልስ እና ሌሴቶን የበታችነት ግምት ሳንሰጥ በኔ ግምት የምድቡ አሸናፊ ለመሆን ፉክክሩ በአልጄሪ እና ኢትዮጵያ መካከል ይሆናል፡፡ የምድቡ ከባድ ተፎካካሪያችን ኢትዮጵያ ነች፡፡ ››

ቢሆንም ቡድናቸው ባሳለፍነው መስከረም ወር አዲስ አበባ ላይ በማሸነፉ አሁንም ይህንኑን ድል እንደሚደግሙ አስታውቀዋል፡፡

“መጋቢት 2016 ወደ አዲስ አበባ ስንመጣ የተሻለ መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡ ከፊታችን የሚጠብቁንን መሰናከሎች በደንብ እናውቃቸዋለን ነገር ግን ለስህተት ቦታ አይኖረንም፡፡ መስከረም ላይ ያመጣነውን ውጤት አዲስ ላይ መድገም ይኖርብናል፡፡”

አሰልጣኙ አያይዘው “ከምድቡ ለማለፍ ጨዋታዎችን ማሸነፍ አለብን በተለይ ከኢትዮጵያ ጋር የምናደርገውን ፡፡ መቶ በመቶ የማሸነፍ ሪከርድ ይዘን ማለፍ ይኖርብናል፡፡”

ያጋሩ