ፕሪሚየር ሊግ ፡ ደደቢት ድቻን አሸንፎ ደረጃውን አሻሻለ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ወደ ሶዶ ያቀናው ደደቢት 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ የደደቢትን ሁለቱም ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ናይጄርያዊው አጥቂ ሳሙኤል ሳኑሚ በፍፁም ቅጣት ምት ነው፡፡ የወላይታ ድቻ ብቸኛ ግብ በ61ኛው ደቂቃ የተገኘችውም በፍፁም ቅጣት ነው፡፡

ደደቢት ድሉን ተከትሎ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ደረጃውን በ2 አሻሽሎ ወደ 6ኛ ደረጃ ሲያሻሽል ድቻ ደግሞ ወደ 7ኛነት አሽቆልቁሏል፡፡

ሊጉን ሲዳማ ቡና በ35 ነጥብ ሲመራ የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የቡናው ቢንያም አሰፋ በ13 ግቦች ይመራል፡፡

ያጋሩ