ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወላይታ ድቻ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-2ወላይታ ድቻ

6′ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን 43′ ቢንያም በላይ| 1′ አላዛር ፋሲካ 83′ በዛብህ መለዮ


ተጠናቀቀ !
የንግድ ባንክና እና በወላይታ ድቻ መካከል የነበረው ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

የተጨዋች ለውጥ ንግድ ባንክ
90′ ፒተር ኑዋድኬ ወጥቶ ጌቱ ረፌራ ገብቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 3

ቢጫ ካርድ – ንግድ ባንክ
89′ ዳንኤል አድሃኖም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!!! ወላይታ ድቻ!!
83′ ፀጋዬ ብርሃኑ ከቀኝ መስመር ያሻገረለት ኳስ በዛብህ በግራ እግሩ ደገፍ አድርጎ አስቆጥሯል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
82′ አማኑኤል ተሾመ ወጥቶ መሳይ አጪሶ ገብቷል

79′ ወላይታ ድቻዎች ጎል ለማስቆጠር በተደጋጋሚ ቢሞክሩም የንግድ ባንክ ተከላካዮች ነቅተው የጎል ክልላቸውን በመጠበቃቸው ሊሳካላቸው አልቻለም፡፡

71′ ተቀይሮ የገባው ዳግም ንጉሴ ከግራ መስመር ሰብሮ በመግባት መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ለጥቂት ቋሚውን ታኮ ወጥቶበታል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
66′ ቢንየያም በላይ ወጥቶ ሲሳይ ዋጆ ገብቷል፡፡

65′ ወላይታ ድቻዎች የአቻነቷን ጎል ለማስቆጠር ጫና ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
63′ ፉአድ ተማም ወጥቶ ዳግም ንጉሴ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ – ንግድ ባንክ
61′ ፍቅረኢየሱስ ተ/ብርሃን ሰአት አባክነሀል በማለት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

52′ እንደ መጀመርያው አጋማሽ ሁሉ በሁለተኛው አጋማሽም በሁለቱ ቡድኖች መካከል ጠንካራ የጨዋታ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
46′ አቤል አበበ ወጥቶ ሳሙኤል ዮሐንስ ገብቷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በንግድ ባንክ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 3

ጎልልል!! ኢትዮ ንግድ ባንክ!!
43′ ቢንያም በላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መሪ የምታደርግ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ቢጫ ካርድ! ወላይታ ድቻ
36′
ሙባረክ ሽኩር የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

34′ አላዛር ፋሲካ ከሳጥን ውጭ አክርሮ የመታውን አማኑኤል ፌቮ እንደምንም ወደ ውጭ አውጥቶበታል፡፡

28′ በግሩም የኳስ ፍሰት ወደ ጎል መድረስ የቻሉት ድቻዎች በአላዛር ፈሲካ አማካኝነት መሪ መሆን የሚችሉበትን የጎል አጋጣሚ አመከኑ፡፡

22′ ጨዋታው በሁለቱም በኩል ግለቱን ጠብቆ በፈጣን በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ቀጥሎ ይገኛል፡፡

12′ ጸጋዬ ብርሃኑ በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኘውን ኳስ የግብ ጠባቂውን አቋቋም ተመልክቶ በግራ እግሩ ቢሞክርም የግቡ አግዳሚ መልሶበታል፡፡

10′ በጨዋታው ነፃ አና ጥሩ የመሸናነፍ ፍላጎት በሁለቱም በኩል እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

ጎልልል!! ኢትዮ ንግድ ባንክ!!
6′ ፍቅረኢየሱስ ተ/ብርሃን ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል፡፡

ጎልልል!! ወላይታ ድቻ!!
1′ በዛብህ መለዮ ከቀኝ መስመር ያሻገረለትን ኳስ አላዛር ፋሲካ በግሩም ሁኔታ ወደ ጎልነት ቀይሮታል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በወላይታ ድቻ አማካኝነት ተጀመረ፡፡


09:00 የዕለቱን ጨዋታውን ከሚመሩት ኮምሽነር እና ዳኞች ጋር በመሆን ጨዋታው ሊጀምር ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ በመግባት ላይ ናቸው፡፡


08:55 በኢትዮ ንግድ ባንክ እና በወላይታ ድቻ መካከል የሚደረገው የ13ኛው ሳምንት የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመርያ ጨዋታ ሊጀመር ሁለቱም ቡድኖች የማሟሟቂያ እንቅስቃሴያቸውን አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡


የመጀመርያ አሰላለፍ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1 – ኢማኑኤል ፌቮ

5 ቶክ ጀምስ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 12 አቤል አበበ 

15 አዲሱ ሰይፋ – 88 ታዲዮስ ወልዴ – 21 ዮናስ ገረመው – 80 ቢኒያም በላይ – 7 ዳንኤል አድሃኖም 

2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን – 11 ፒተር ንዋድኬ

ተጠባባቂዎች
29 ሙሴ ገብረኪዳን
14 ሲሳይ ዋጆ
44 ሞላለት ያለው
19 ፍቃዱ ደነቀ
26 ጌቱ ረፌራ
17 ሳሙኤል ዮሃንስ
99 ዳንኤል ለታ


የመጀመርያ አሰላለፍ – ወላይታ ድቻ

1 ወንድወሰን አሸናፊ

7 አናጋው ባደግ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 2 ፈቱዲን ጀማል – 20 አብዱልሰመድ አሊ

4 ዮሴፍ ድንገቱ – 8 አማኑኤል ተሾመ – 23 ጸጋዬ ብርሃኑ

17 በዛብህ መለዮ – 19 አላዘር ፋሲካ – 11 ፉአድ ተማም

ተጠባባቂዎች
99 ወንድወሰን ገረመው
24 ተክሉ ታፈሰ
5 ዳግመም ንጉሴ
3 ቶማስ ስምረቱ
10 እንዳለ መለዮ
13 ዳግም በቀለ
26 መሳይ አንጪሶ


ሠላም እንደምን ውላችኋል ውድ አንባቢዎቻችን። በ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወላይታ ድቻ በአአ ስታድየም የሚያደርጉትን ጨዋታ እንደተለመደው በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት የጨዋታውን ዋና ዋና ክንውኖች የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

Leave a Reply