መከላከያ ከ ፋሲል ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTመከላከያ  2 2 ፋሲል ከተማ

 35′ ማራኪ ወርቁ | 28′ 66′ አብዱርሀማን ሙባረክ

85′ ሳሙኤል ታዬ

____________________________

ጨዋታው 2 2 በሆነ የአቻ ውጤት ፍፃሜውን አግኝቷል !
90+6 ኤርሚያስ ሐይሉ ከመከላከያዎች ሳጥን ጠርዝ ላይ የመታውን ኳስ አቤል አድኖታል ። አቤል ቡድኑን ከሽንፈት ታድጓል ።

90+2 ፋሲሎች የቀረውን ሰዐት ለመጠቀም እያጠቁ ይገኛሉ ። ምንይሉ ወንድሙን በቀይ ካርድ ያጡት መከላከያዎች ውጤቱን ማስጠበቅ የፈለጉ ይመስላሉ ። 

90’+1  የተጨዋች ለውጥ መከላከያ

ኡጉታ ኦዶክ ሳሙኤል ሳሊሶን ቀይሮ ገብቷል

90′ ጭማሪ ደቂቃ 5 !

86′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ

ሚካኤል ደስታ በ ቴውድሮስ ታፈሰ ተቀይሮ ወጥቷል ።

85 ‘ ጎል መከላከያ !!! ሳሙኤል ታዬ

በግራ መስመር መከላከያዎች በሰነዘሩት ጥቃት ከሞክሼው ሳሙኤል ሳሊሶ የተሻገረለትን ኳስ አንድ ጊዜ ገፍቶ በመምታት ሳሙኤል ታዬ ቡድኑን አቻ አድርጓል ።

82′ ፋሲሎች በሁለቱ መስመሮች በፈጣን የማጥቃት ሽግግር በመታገዝ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ ። 

78′ ኤዶም ኮርዶ ከሰዒድ ሁሴን የተቀበለውን ኳስ በግራ በኩል ይዞ ለመግባት ቢሞክርም አቤል ማሞ ፈጥኖ በመውጣት አድኖበታል ።

77′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከመሀል ሜዳ የመታውን የቅጣት ምት ፋሲሎች ከመለሱ በኋላ በመልሶ ማጥቃት 5-2 ሆነው የጦሩ ሜዳ ላይ ቢገቡም አብዱርሀማን ኳስ ለመቆጣጠር ያረገው ሙከራ ሳይሳካለት አጋጠሚው አልፏቸዋል ።

73′ ጨዋታው ወደመጀመሪያው ጥሩ መንፈሱ የተመለሰ ይመስላል ። መከላከያዎች አቻ ለመሆን ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ነው ። አፄዎችም የመልሶ ማጥቃት እድሎችን ለመጠቀም እየሞከሩ ነው ።

66′ ጎል  ፋሲል ከተማ !!! አብዱርሀማን ሙባረክ

 ሔኖክ ገምቴሳ ከመሀል ሜዳ በአየር ላይ የላከለትን ድንቅ ኳስ ተጠቅሞ አብዱርሀማን በግንባሩ በመግጨት አቤልን ካለፈ በኋላ በግራ እግሩ ለራሱ እና ለቡድኑ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሯል ። 

65′ መከላከያዎች በግራ መስመር ተደጋጋሚ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው።  አልተጠቀሙበትም እንጂ የቅጣት እና የማዕዛን ምቶችንም አግኝተው ነበር ።

62′ የተጨዋች ለውጥ ፋሲል ከተማ

ሰለሞን ገ/ መድህን መጥቶ ኤፍሬም አለሙ ሲገባ ፍቅረሚካኤል ዓለሙም ይስሀቅ መኩሪያን ተክቶታል ።

60′ ጨዋታው ቀጥሏል ። ኤዶም ከቀኝ መስመር የተላከለትን ጥሩ ኳስ ሳይደርስበት ወደውጪ ወጥቶበታል። 

58′ መከላከያዎች በቀይ ካርዱ ምክንያት ይመስላል ክስ እያስያዙ ነው። ጨዋታው በዚህ ምክንያት ተቋርጧል 

53′ ጨዋታው የመጀመሪያ ግማሽ ውበቱን ያጣ ይመስላል ። የዳኛ ፊሽካም በዝቶበት በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ይገኛል። 

50′ ቀይ ካርድ ! መከላከያ ምንይሉ ወንድሙ

ምንይሉ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ሲወድቅ ዳኛው ሆን ብለህ ነው በሚል ለፋሲሎች ቅጣት ምት ሲሰጡ በፈጠረው ሰጣገባ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ ተመልክቶ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል ።

48′ እንደመጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ አሁንም መሀል ሜዳ ላይ ጉሽሚያዎች በርክተዋል ።

46′ ሁለተኛው አጋማሽ በፋሲል ከተማዎች ተጀመረ ።

የመጀመሪያው ግማሽ ሁለት ግቦችን እና አዝናኝ ጨዋታን አሳይቶን ተጠናቋል ።

45′ ጭማሪ ደቂቃ 2 !

44′ ኤርምያስ ሐይሉ ቅጣት ምት ለመደረብ ያላግባብ በመጠጋቱ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ። ቅጣት ምቱም የፋሲሎች ሳጥን ውስጥ በበሀይሉ ግርማ በጭንቅላት ተገጭቶ የፋሲል ተከላካዮች አውጥተውታል ። ይህንን ኳስ ፋሲሎች በመልሶ ማጥቃት ይዘው ቢሄዱም አልተጠቀሙበትም። 

41′ መከላከያዎች በድንቅ መልሶ ማጥቃት ተጋጣሚያቸው ሳጥን ውስጥ ቢገቡም ከጨዋታ ውጪ ሆነው ዕድሉን ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል ።

38′ ሰለሞን ገ/መድህን በምንይሉ ወንድሙ ላይ በሰራው ጥፋት ሁለተኛውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመለከተ ።

37′ ምንይሉ ወንድሙ ዳኛው የቅጣት ምት ቢሰጡትም ከይስሀቅ መኩሪያ ጋር ግብ ግብ ለመፍጠር በመሞከሩ የመጀመሪያውን ቢጫ ካድ ተመልክቷል ።

35′ ጎል መከላከያ !!! ማራኪ ወርቁ
ሳሙኤል ታዬ ከመሀል ሜዳ ያሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ ተከላካዮችን በመቅደም ማራኪ ወርቁ ጦሩን አቻ አድርጓል ።

33′ ሰለሞን ገ/መድህን ከመሀል ያሾለከለትን ኳስ ይዞ ለመግባት የሞከረው ኤዶም ኮድዞ በመከላከያው ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ ተቀድሞ ተመልሶበታል።

28′ ጎል  ፋሲል ከተማ !!! አብዱርሀማን ሙባረክ

ሶስቱ የፋሲል ከተማ የፊት አጥቂዎች ኤርሚያስ ኤዶም እና አብዱርሀማን ከሳጥን ውጪ ያደረጉት ቅብብል በመጨራሻ በአብዱርሃማን የከረረ ምት ወደ ግብነት ተቀይሯል ። ግሩም ጎል !

25′ ፋሲል ከትልማዎች ከመሀል ሜዳ ግራ መስመር ላይ ያገኙትን የቅጣት ምት ሔኖክ ገምቴሳ በቀጥታ አሻማው ተብሎ ሲጠበቅ ለኤርምያስ ሐይሉ አሾልኮለት ኤርሚያስ ወደውስጥ ቢያሻማም ወደውጪ ወጥቷል።

20′ ጨዋታው ተደጋጋሚ ጉሽሚያዎች እየተስተዋሉበት ነው ። የወጌሻዎችን እርዳታ የጠየቁ ቀላል ግጭቶችን እየተመለከትን እንገኛለን ።

16′ ሽመልስ ተገኝ ከመሀል ሜዳ ቀኝ መስመር ላይ ያሻማለትን ኳስ ምንይሉ ወንድሙ በግንባሩ አስቆጠረ ሲባል ኳሷን ሳይነካት ወደውጪ ወጣች ። የቀኝ መስመር ተከላካዩ ግሩም ዕድል ፈጥሮ ነበር !

12′ የፋሲሉ ግብ ጠባቂ  ምንተስኖት አደጎ ሳሙኤል ታዬን ለማለፍ ሞክሮ ሳሙኤል ኳሱን ቀምቶ ወደግብ ቢሞክርም ኳስ ለጥቂት በጎን ወጥታለች። ከባድ ስህተት ነበር !

11′ ኤርሚያስ ሐይሉ ከቀኝ መስመር የላከለትን ኳስ በግራ መስመር ላይ ነፃ የነበረው ሔኖክ ገምቴሳ ከመቆጣጠሩ በፊት አቤል ደርሶ አውጥቶታል ።

10′ ጨዋታው በፋሲሎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በመከላከያዎች ሜዳ ላይ አመዝኖ ቀጥሏል ።

6′ ሽመልስ ተገኝ ከመሀል ሜዳው ጠጋ ብሎ የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ ሲመታ ግብጠባቂው ምንተስኖት አደጎ ጨርፎት እና የግቡ አግዳሚ መልሶት ጎል ሳይቆጠር ቀርቷል ።

3′ ፋሲል ከተማዎች ኳስ ተቆጣጥረው ወደተጋጣሚያቸው ሜዳ ለመግባት እየሞከሩ ነው ። ባለሜዳዎቹም ተረጋግተው በራሳቸው ሜዳ ላይ ኳስ የማስጣል እና ፈጠን ብሎ ወደፊት መሄድን አጨዋወት የመረጡ ይመስላሉ ።

1′ ጨዋታው በመከላከያዎች አማካይነት ተጀምሯል ።

የፋሲል ከተማ አሰላለፍ

1 ምንተስኖት አደጎ

13 ሰኢድ ሁሴን –  16 ታደለ ባይህ – 14 ከድር ኸይረዲን – 21 አምሳሉ ጥላሁን                                               

17 ይስሀቅ መኩሪያ – 26 ሔኖክ ገምተሳ – 27 ሰለሞንገ/መድህን

99 ኤርምያስ ሃይሉ – 94 ኤዶም ኮሮዞ – 18 አብዱርህማን ሙባረክ

ተጠባባቂዎች

31 ቴውድሮስ ጌትነት

7 ፍፁም ከበደ

3 ሱሌይማን አህመድ

4 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ

25 ኤፍሬም ዓለሙ

20 ናትናኤል ጋንቹላ

10 ሙሉቀን ታሪኩ


የመከላከያ አሰላለፍ

1 አቤል ማሞ

2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 4 አወል አብደላህ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ 

19 ሳሙኤል ታዬ – 21 በሀይሉ ግርማ – 13 ሚካኤል ደስታ – 9 ሳሙኤል ሳሊሶ

7 ማራኪ ወርቁ – 14 ምንይሉ ወንድሙ

ተጠባባቂዎች

22 ይድነቃቸው ኪዳኔ

17 ምንተስኖት ከበደ

11 ካርሎስ ዳምጠው

15 ቴዎድሮስ ታፈሰ

10  የተሻ ግዛው

26 አጉታ ኦዶክ

23. መስፍን ኪዳኔ

11፡ 25 በመቀጠል የሁለቱን ቡድኖች አሰላለፍ እናቀርብላችኋለን ።

11፡20 ቡድኖቹ አሟሙቀው ጨርሰው ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል ።

የሁለቱን ቡድኖች ወቅታዊ ውጤቶች ስንመለከት 10ኛው ሳምንት ላይ በሜዳው በአርባምንጭ ከተማ 2 – 1 የተሸነፈው መከላከያ ከዚያ በመቀጠል አዲስ አበባ ላይ ከደደቢት እንዲሁም ድሬደዋ ላይ ከ ድሬደዋ ከተማ ነጥብ መጋራቱ የሚታወስ ነው ። በ12ተኛው ሳምንት ሜዳው ላይ በደደቢት የ 1 – 0 ሽንፈት የቀመሰው ፋሲል ከተማ ደግሞ በ11ኛው ሳምንት አርባምንጭ ላይ ከ አንባምንጭ ከተማ ተጫውቶ አንድ ነጥብ ይዞ የተመለሰ ሲሆን 10ኛው ሳምንት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 0 ማሸነፍ ችሎ ነበር።

11 ፡ 10 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛሉ ። እንደተለመደውም የፋሲል ከተማ ደጋፊዎች በብዛት ተገኝተው በዝማሬ ስታድየሙን እያደመቁ ይገኛሉ ።

ሠላም ውድ የሶከር ኢትዮጵያ ተከታታዮች ። አሁን ደግሞ የ13ተኛው ሳምንት እና የእለቱን ሶስተኛ ጨዋታ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ልናስነብባችሁ ተዘጋጅተናል ። በጨዋታውም መከላከያ ፋሲል ከተማን በአዲስ አበባ ያስተናግዳል ። ባለሜዳው መከላከያ በሊጉ 17 ነጥቦችን ሰብስቦ 7ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፋሲል ከተማም አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው በ 19 ነጥቦች 5ተኛ ደረጃን ይዟል።

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !


1 Comment

  1. ከተጫዋቾች አሰላለፍ ጋር፣ የዳኞቹም አሰላለፍ (ሥም ዝርዝር ቢጠቀስ)ለግድግዳቹ ተመልካች (አንባቢ) መልካም ነው እላለሁ፡፡ የአሰላለፍ አገላለጻችሁን እባካችሁ ሙሉዕ አድርጉልን? እስካሁንም ባለንበት ለምታደርሱን ወቅታዊ መረጃ ግን እናመሰግናለን! በርቱ!

Leave a Reply