ፊፋ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በፊፋ ወርሃዊ የደረጃ ሰንጠረዥ 101ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ዋልያው ባለፈው ወር 100ኛ ደረጃ ላይ የነበረ ሲሆን በዚህ ወር 1 ደረጃ ወርዷል፡፡
ግብፅ ፕሪሚየር ሊግ
ለግብፁ ዋዲ ዴግላ የሚጫወተው የብሄራዊ ቡድኑ ኮከብ ሳላዲን ሰኢድ ትላንት ምሽት በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ በዛማሌክ 3-2 በተሸነፉበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ ወጥቷል፡፡ ጉዳቱ ከ3 ሳምንት እስከ 1 ወር ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ተነግሯል፡፡
የኢትዮጵያ ዋንጫ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ሁለተኛ ቀን ውሎው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፈበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ፈረሰኞቹ ሲዳማ ቡናን 1-0 ሲረቱ ብቸኛዋን ግብ ኡመድ ኡኩሪ በ89ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡ በግማሽ ፍፃሜው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሙገር ሲሚንቶ መከላከያ ደግሞ ከደደቢት እና ንግድ ባንክ አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2ኛ ዙር ጨዋታዎች ፕሮግራም
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ዙር ከ5 ቀናት እረፍት በኋላ ቅዳሜ ይጀመራል፡፡ የ14ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ፕሮግራም እነዚህን ይመስላሉ…
ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2006
ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (09፡00 ፡ ቦዲቲ)
መብራት ኃይል ከ ሀዋሳ ከነማ (11፡00 ፡ አአ ስታድየም)
እሁድ ሚያዝያ 5 ቀን 2006
ሐረር ቢራ ከ ዳሽን ቢራ (09፡00 ፡ ሐረር)
አርባምንጭ ከነማ ከ ኢትዮጵያ መድን (09፡00 ፡ አርባምንጭ )
ሲዳማ ቡና ከ መካላከያ (09፡00 ፡ ይርጋለም)
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሙገር ሲሚንቶ (11፡00 ፡ አአ ስታድየም)
ማክሰኞ
ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት (11፡00 ፡ አአ ስታድየም)