ፕሪምየር ሊግ፡ ደደቢት ከመከላከያ ላልታወቀ ጊዜ ተራዘመ

በኢትዮጵያ ፕሪምር ሊግ 18ኛ ሳምንት ሊካሄድ የነበረው ደደቢት እና መከላከያ ጨዋታ ላልታወቀ ጊዜ መዛወሩን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን አስታውቋል፡፡ የመከላከያው መሃል ሜዳ ተጫዋች ተክለወልድ ፍቃዱ ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ በስነ-ልቦናው ረገድ የጦሩ ተጫዋቾች እስኪረጋጉ ጨዋታው ላልታወቀ ጊዜ ተላልፏል፡፡ የመከላከያው አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ቅዳሜ ዕለት ከፋና 98.1 ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ ቡድናቸው ከደደቢት ጋር መጫወት እንደሚያስቸግረው ገልፀው ነበር፡፡ ሌሎች የ18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተያዘላቸው መርሃ ግብ እንደሚካሄዱ ፌድሬሽኑ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

ያጋሩ