ሀዋሳ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

​​FTሀዋሳ ከተማ  0-0 ድሬዳዋ ከተማ


ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 3 ደቂቃ


89′ የሀዋሳ ከተማ ደጋፊ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን እየተቃወመ ነው።


88′ ደስታ ዮሀንስ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ዮናታን አግኝቶ ወደግብ መቀየር አልቻለም። የሚያስቆጭ አጋጣሚ።


87′ ታፈሰ ሰለሞን የዳኛውን ውሳኔ በመቃወሙ የማስጠንቀቂያ ካርድ አይቷል።


85′ ጋዲሳ መብራቴ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ዮናታን ከበደ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ወጥቶበታል።


78′ የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ ከተማ

ኤፍሬም ዘካሪያስ ወጥቶ እስራኤል እሸቱ ገብቷል።


77′ የተጫዋች ለውጥ – ድሬዳዋ ከተማ

ሀብታሙ ወልዴ ወጥቶ ዘሪሁን አንሼቦ ገብቷል።


76′ ሀብታሙ ወልዴ ያቀበለውን ኳስ በረከት ይሳቅ በቀላሉ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ በሚገርም ሁኔታ ወደ ላይ ሰዶታል።


74′ ታፈሰ ሰለሞን አሾልኮ ያቀበለውን ኳስ ፍርዳወቅ መትቶ በሚያስገርም ሁኔታ ሳምሶን አዳነበት።


72′ ሀብታሙ ወልዴ ኳሱን እየገፋ ወደ አደጋ ክልሉ ገብቶ ከግብ ጠባቂው ጋር ቢገናኝም ሱሆሆ ሜንሳህ ከእግሩ ላይ ነጠቆታል።


70′ ታፈሰ ሰለሞን በሳጥኑ ውስጥ ተጠልፌያለሁ ብሎ ሲወድቅ ዳኛው ፍፁም ቅጣት ምት ሳይሰጡ በማለፋቸው ከደጋፊዎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።


67′ ዮናታን ከበደ በግንባሩ አመቻችቶ የሰጠውን ኳስ ኤፍሬም ዘካሪያስ ሊጠቀምበት አልቻለም።


64′ ሀዋሳ ከተማዎች ግብ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራዎች እያደረጉ ነው።


62′ በረከት ሳሙኤል በጋዲሣ መብራቴ ላይ ጥፋት በመፈፀሙ ቢጫ ካርድ አይቷል።


60′ የተጫዋች ለውጥ – ድሬዳዋ ከተማ

ይሁን እንደሻው ወጥቶ ረመዳን ናስር ገብቷል።


53′ ፍሬው ሰለሞን ተቀይሮ ሲወጣ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በመቃወም ከግቢ በቀጥታ የወጣ ሲሆን ዳኛውም ባልተገባ ባህሪ ቢጫ ካርድ ሰጥተውታል።


53′ የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ ከተማ

ተደጋጋሚ ግቦችን ያመከነው ፍሬው ሰለሞን ወጥቶ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኃላ የተመለሰው ዮናታን ከበደ ገብቷል። 


52′ ፍሬው ሰለሞን አሁንም ያገኘውን ኳስ በቄንጠኛ ሁኔታ ለማግባት ሲሞክር ሳምሶን ይዞበታል። ሀዋሳ ከተማዎች በሁለተኛው አጋማሽ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን እያደረጉ ነው።


49′ ፍሬው ሰለሞን ከጋዲሳ በረጅሙ የተላከለትን ኳስ በድጋሚ ሊጠቀምበት አልቻለም። 


46′ ሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ ፍሬው ሰለሞን አራት ተጫዋቾችን አልፎ ወደ ሳጥን በመግባት ወደግብ ቢመታም ኳሱ ከግቡ አግዳሚ በላይ ወጥቶበታል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።


የመጀመሪያው አጋማሽ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 3 ደቂቃ


40′ የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ሶሆሆ ሜንሳ ተጎድቶ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።


37′ የተጫዋች ለውጥ – ድሬዳዋ ከተማ

ኤርሚያስ በለጠ ወጥቶ አልሳሀኒ አልማሀዲ ገብቷል።


32′ ሀዋሳ በፍርዳወቅ ሲሳይ አማካይነት ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ በሚል ግቡ ተሽሯል። ደጋፊውም የዳኛውን ውሳኔ በመቃወም ድምፁን አሰምቷል።


27′ ፍሬው ሰለሞን ያቀበለውን ኳስ ጋዲሳ ከርቀት አክርሮ መትቶ ሳምሶን አሰፋ ዳግም አወጣበት። ሀዋሳዎች ተደጋጋሚ ሙከራ እያደረጉ ነው።


23′ ሀዋሳ ከተማዎች ጫና ፈጥረው ቢጫወቱም ያገኟቸውን እድሎች መጠቀም አልቻሉም።


22′ ጋዲሳ መብራቴ ከ25 ሜትር ርቀት የመታውን ኳስ ሳምሶን አወጣው፡፡


20′ የግብ ጠባቂው ሜንሳህን መውጣት አይቶ ከመሀል አጋማሽ የመታው ኳስ ወደ ውጭ ወጣ፡፡


18′ ዳንኤል ደርቤ ከቀኝ መስመር አሻግሮ ፍርዳወቅ ሲሳይ በቀላሉ አመከነው፡፡


14′ ፍርዳወቅ ሲሳይ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ፍሬው ሰለሞን አግኝቶ ሀዋሳን መሪ አደረገ ሲባል በግቡ ቀኝ ቋሚ ነክታ ወጣች፡፡


6′ ፍሬው ሰለሞን በግል ጥረቱ እየገፋ ገብቶ ያቀበለውን ኳስ ታፈሰ ሰለሞን ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ሳይጠቀምበት ቀረ፡፡


3′ ፍሬው ከደስታ ዮሀንስ የተሻገረለትን ኳስ አክርሮ መቶ ግብ ጠባቂው ሳምሶን በሚገርም ሁኔታ አውጥቶበታል፡፡


1′ ዘነበ ከበደ ከመአዘን ምት ያሻማውን ኳስ ሀብታሙ ወልዴ ሳይጠቀምበት ቀረ


ተጀመረ!!


ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ አማካኝነት ተጀመረ፡፡


የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ 

1 ሶሆሆ ሜንሳህ

7 ዳንኤል ደርቤ – 13 መሳይ ጳውሎስ – 22 መላኩ ወልዴ – 12 ደስታ ዮሀንስ

24 ኃይማኖት ወርቁ – 3 ኤፍሬም ዘካርያስ
5 ታፈሰ ሰለሞን – 10 ፍሬው ሰለሞን – 11 ጋዲሳ መብራቴ

27 ፍርዳወቅ ሲሳይ


ተጠባባቂዎች

30 አላዛር መርኔ

4 አስጨናቂ ሉቃስ

8 ግርማ በቀለ

9 እስራኤል እሸቱ

6 አዲስአለም ደበበ

16 ዮናታን ከበደ

ነጋሽ ታደሰ


የድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ

1. ሳምሶን አሰፋ

2′ ዘነበ ከበደ – 4 ተስፋዬ ዲባባ –  15 በረከት ሳሙኤል – 14 ኄኖክ አዱኛ

24 አሳምነው አንጀሎ – 6 ይሁን እንዳሻው – 12. ኤርሚያስ በለጠ – 25 ዘላለም ኢሳያስ

18 በረከት ይስሀቅ – 16 ሀብታሙ ወልዴ
 


ተጠባባቂዎች 

23 ቢንያም ሐብታሙ 

19 ፍቃዱ ወርቁ

28 አልሳሃሪ አልማሃዲ

10 ረመዳን ናስር

27 ዘርአይ ገ/ስላሴ

3 ሮቤል ግርማ

5 ዘሪሁን አንሼቦ

Leave a Reply