ማርያኖ ባሬቶ ከዋልያዎቹ አሰልጣኝነታቸው በይፋ ተነሱ

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋነና አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ በይፋ ከዋና አሰልጣኝነት ቦታቸው መነሳታቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ዛሬ እንዳስታወቀው የፌዴሬሽኑ እና የባሬቶ ሰምምነት ከ12 ቀናት በኋላ (ኤፕሪል 30) እንዲቋረጥ ተወስኗል፡፡ በስምምነቱ መሰረትም የ3 ወር ደሞዛቸው 54 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በካሳ መልክ የሚያገኙ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም አሰልጣኘ ከፌዴሬሽኑ ጋር ያለቸው የአሰልጣኝነት ውል ቢቋጭም ወደፊት በወጣቶች ስልጠና ላይ ከፌዴሬሽኑ ጋር በትብብር እንደሚሰሩም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨምሮ አስታውቀል፡፡

 

ያጋሩ