የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዙር ሊጠናቀቅ የ2 ሳምንታት እና ተስተካካይ ጨዋታዎች ብቻ ቀርተውታል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንም የሁለተኛው ዙር መቼ እንደሚጀመር ከወዲሁ አስታውቋል፡፡
የሊጉ 1ኛ ዙር መደበኛ ጨዋታዎች ጥር 29 ሲጠናቀቁ የካቲት 2 ተስተካካይ ጨዋታዎች ተደርገው 1ኛው ዙር ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል፡፡ ከ5 ቀናት በኋላ ደግሞ የፕሪምየር ሊጉ 1ኛ ዙር ግምገማ ፣ ሪፖርት እና ውይይት በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚደረግ ሲሆን ከ17 ቀናት በኋላ የካቲት 19 ቀን 2009 የ2ኛ ዙር እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ ያወጣው መርሃ ግብር ያሳያል፡፡ በ1ኛው ዙር እረፍት መሃከልም የኢትዮጵያ ጥሎማለፍ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
የሊጉ 14ኛ ሳምንት ጥር 22 እና 23 ፣ የ15ኛ ሳምንት ጥር 28 እና 29 እንዲሁም በንግድ ባንክ እና ሀዋሳ ከተማ ፣ በፋሲል ከተማ እና ወላይታ ድቻ መካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች የካቲት 2 ይደረጋሉ፡፡
© በድረገፁ የሚወጡ ፅሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሰ በቀር ሙሉ ለሙሉ የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ ፅሁፎቹን በሌላ ሚድያ ሲጠቀሙ ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡