​ከፍተኛ ሊግ | ኢትዮጵያ መድን ሲያሸንፍ ውሃ ስፖርት እና ሱሉልታ ነጥብ ተጋርተዋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 10ኛ ሳምንት ዛሬ አበበ ቢቂላ ላይ በተደረጉ 2 የምድብ ሀ ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡ ኢትዮጵያ መድን ድል ሲያስመዘግብ ውሃ ስፖርት እና ሱሉልታ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

08:00 ላይ ቡራዩ ከተማን ያስተናገደው ኢትዮጵያ መድን ከእረፍት በፊት እና በኃላ በተቆጠሩ ሁለት ሁለት ግቦች 4-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ 

ጀማል አህመድ ገና በ5ኛው ደቂቃ መድንን ቀዳሚ ሲያደርግ አብይ ቡልቲ በ28ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን አክሎ በመድን 2-0 መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
ከእረፍት መልስ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና አአ ከተማ አማካይ ሐብታሙ ረጋሳ እና ተቀይሮ የገባው አስራት ሸገሬ ተጨማሪ ግቦች አክለው ጨዋታው በሰማያዊዎቹ 4-0 አሸናፊነት ተደምድሟል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ መድን በ15 ነጥብ ደረጃውን ወደ 4 ከፍ ሲያደርግ ቡራዩ ከተማ በ13 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

10:00 ላይ በኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት እና ሱሉልታ ከተማ መካከል የተካሄደው ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ሱሉልታ ሁለት ጊዜ የመምራት እድል ባገኘበት ጨዋታ መጨረሻ ከፍተኛ ውዝግብ ተከስቷል፡፡
ሱሉልታ ከተማ በአምበሉ አቤል ታሪኩ የቅጣት ምት ግብ ለረጅም ደቂቃዎች መሪ መሆን ችሎ ነበር፡፡ ሳሙኤል ወንድሙ ባለ ሜዳዎቹን አቻ ማድረግ ቢችልም ሱሉልታዎች በይድነቃቸው የሺጥላ ግብ በድጋሚ መሪ መሆን ችለዋል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ  የሽርፍራፊ ደቂቃዎች እድሜ ሲቀረው ደሳለኝ ወርቁ ለውሃ ስፖርት ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው መሃል በተደጋጋሚ ሲታይ የነበረው ጉሽሚያ እና ሽኩቻ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም አይሎ የሁለቱ ቡድን አባላት ጸብ ውስጥ የገቡ ሲሆን የመጫወቻው ሜዳ በተመልካቾች እና የጸጥታ ሃይሎች ተወሮ ተስተውሏል፡፡ እንዲህ አይነት ወሰን ያጡ ጠቦች በሊጎቻችን እየተለመዱ መምጣታቸው አሳሳቢ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡


የከፍተኛ ሊጉ ነገ ሲቀጥል በመላ ሃገሪቱ 14 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም እንደተለመደው ጨዋታዎች በቀጥታ የውጤት መግለጫ ወደ እናንተ ታደርሳለች፡፡ ምድብ ሀ

ቅዳሜ ጥር 20 ቀን 2009
FTኢት መድን4-0ቡራዩ ከተማ
FTኢት ውሃ ስፖርት2-2ሱሉልታ ከተማ
እሁድ ጥር 21 ቀን 2009
ባህርዳር ከተማ08:00ወልዋሎ አ.ዩ.
ለገጣፎ ለገዳዲ09:00ሽረ እንዳስላሴ
አክሱም ከተማ09:00አአ ፖሊስ
ሰ.ሸ.ደ. ብርሃን09:00ሰበታ ከተማ
ወሎ ኮምቦልቻ09:00መቐለ ከተማ
አማራ ውሃ ስራ10:00አራዳ ክ.ከ

ምድብ ለ

እሁድ ጥር 21 ቀን 2009
ደቡብ ፖሊስ09:00ድሬዳዋ ፖሊስ
ጅማ ከተማ09:00ካፋ ቡና
ጂንካ ከተማ09:00ፌዴራል ፖሊስ
አርሲ ነገሌ09:00ስልጤ ወራቤ
ወልቂጤ ከተማ09:00ሻሸመኔ ከተማ
ዲላ ከተማ09:00ሀዲያ ሆሳዕና
ነገሌ ቦረና09:00ሀላባ ከተማ
ናሽናል ሴሜንት10:00ነቀምት ከተማ

 

Leave a Reply