U-20 ፕሪምየር ሊግ | በዛሬ ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አካዳሚ አሸንፈዋል

ለመጀመርያ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጀ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል፡፡ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው ኒያላ ሜዳ ዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎችም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አሸንፈዋል፡፡

ቀትር 6:00 ላይ በደደቢት እና ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ መካከል የተደረገው ጨዋታ አካዳሚ በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠረች ብቸኛ ግብ 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ የአካዳሚን የድል ግብ በ10ኘው ደቂቃ ያስቆጠረው ኤሌክሳደር አወት ነው፡፡

በዕለቱ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አምበል እና አጥቂ አሌክሳደር አወት ፤ ከደደቢት የግራ መስመር ተከላካዩ ማቲዎስ ሰፋ ያሳዩት ግሩም እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ ነበር።

09:00 ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስና በመከላከያ መካከል የተካሄደው ጨዋታ ሳቢና ማራኪ እንዲሁም ድራማዊ የሆነ ክስተት አስተናግዶ በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በመጀመርያው አጋማሽ ብልጫ የነበራቸው ፈረሰኞቹ በ18ኛው ደቂቃ ተስፋዬ በቀለ እና በ32ኛው ደቂቃ እንደልቡ ደሴ ባስቆጠሩት ጎል 2-0 በመምራት እረፍት ሲወጡ ከእረፍት መልስ መከላከያዎች ተሻሽለው በመቅረብ ከመመራት ተነስተው አብነት ይግለጡ በ62ኛው ደቂቃ በጨዋታ ፣ 75ኛው ደቂቃ ላይ በፍ/ቅ/ም አብነት ባስቆጠራቸው ጎሎች አቻ መሆን ችለው ነበር፡፡ በመጨረሻም የዳኛው የማጠናቀቂያ ፊሽካ ሲጠበቅ በዕለቱ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የዋለው እንደልቡ ደሴ ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ አሸናፊ የምታደርገውን 3ኛ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል

በሁለቱ በድኖች ጨዋታ ከመከላከያ አጥቂው በኃይሉ ኃ/ማርያም በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል እንደልቡ ደሴ ያሳዩ የነበረው ጥሩ እንቅስቃሴ በዕለቱ የነበረውን ተመልካች የሳበና ልብ ተስፋ ሰጪ ነበር፡፡

የነገ ጨዋታዎች

05:00 ኢትዮ ኤሌትሪክ ከ አዳማ ከተማ [ኤሌክትሪክ ሜዳ ፣ ጎፋ]

05:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ [ባንክ ሜዳ ፣ ሲኤምሲ]

05:00 ኢትዮጵያ መድን ከ ሀዋሳ ከተማ [መድን ሜዳ ፣ ቃሊቲ]

09:00 ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ [ሶዶ]

የደረጃ ሰንጠረዥ

U-20 ሰንጠረዥ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
121142547222544
221124536191740
320113633221136
42189432201233
5209562626032
6217771718-128
7216691529-1424
8206591620-423
92156102035-1521
102062121730-1320
112131081827-919
12213991524-918

Leave a Reply