የእሁድ ዜናዎች

ዛሬ ጠዋት የተወሩ አጫጭር ወሬዎችን እንዲህ አቅርበናቸዋል (የዜናዎቹ ምንጭ ፕላኔት ስፖርት ነው)

-ጎራን ስቲቫኖቪች ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከነገ ጀምሮም ከፌዴሬሽኑ ጋር ድርድር ያደርጋሉም ተብሏል፡፡

– በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ሐረር ቢራ ታጋይ አማረን አስፈርሟል፡፡ የግራ መስመር ተጫዋቹ ታጋይ ከዚህ ቀደም ለአርባምንጭ ጨጨ እና ውሃ ስፖርት ተጫውቷል፡፡

-አሸናፊ አደም ዳሸን ቢራን መቀላቀሉ ተወርቷል፡፡ አጥቂው ሲዳማ ቡናን ለቆ ወደ ደደቢት የተዘዋወረው በክረምቱ መስኮት እንደነበር ይታወሳል፡፡

-መስፍን አህመድ ‹‹ጢቃሶ›› ንግድ ባንክን ለቆ ለብሄራዊ ሊጉ ሰበታ ከነማ ፈርሟል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን አምበል በንግድ ባንክ ለ2 አመት ከ6 ወር ቆይቷል፡፡

-በኢትዮጵያ ቡና የክረምቱ የተጫዋቾች መልቀቅ ድራማ በቀጣዩ ክረምትም የሚደገም ይመስላል፡፡ የክለቡ ዋና ተሰላፊዎችን ጨምሮ 14 ተጫዋቾች የኮንትራታቸው ውል ሰኔ መጨረሻ ላይ ያበቃል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ