ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTኢትዮጵያ ቡና 5-2 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

31′ 85′ ሳሙኤል ሳኑሚ 49′ 59’አስቻለው ግርማ 64′ ጋቶች ፓኖም (ፍቅም) | 72′ ፒተር ኑዋዲኬ (ፍቅም) 87′ አምሃ በለጠ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 5-2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በ2009 የውድድር ዘመን ከፍተኛው የግብ መጠን የተመዘበበት ጨዋታም ሆኗል፡፡

90+5′ ፒተር የመታውን ቅጣት ምት ሀሪሰን አውጥቶበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
90′
ኤልያስ ማሞ ወጥቶ አብዱልከሪም ሀሰን ገብቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 5

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
88′
እያሱ ታምሩ ወጥቶ ሳለአምላክ ተገኝ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! ባንክ!!!!
87′ ፒተር የመታውን ኳስ ሀሪስን ሲተፋው በቅርብ ርቀት የነበረው አምሃ በለጠ አግኝቶ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ጎልልል!!!! ቡና!!!
85′ ሳሙኤል ሳኑሚ ከተከላካይ ነጥቆ በግብ ጠባቂው ሙሴ ገብረኪዳን አናት በመስደድ ድንቅ ጎል አስቆጥሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
79′
አስቻለው ግርማ (ጉዳት) ወጥቶ ያቡን ዊልያም ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
78′
ወንድይፍራው ጌታሁን በፒተር ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ አህመድ ረሺድም ቢጫ ካርድ አይቷል፡፡

75′ እያሱ ከቶክ ቀምቶ ለኤልያስ አቀብሎ ኤለልያስ ለአስቻለው ግልጽ የግብ እድል ቢፈጥርለትም የመታውን ኳስ ሙሴ ገብረኪዳን አድኖበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
73′
ሳሙኤል ሳኑሚ የማስጠንቀቂያ ካርደድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!! ባንክ !!!
72′ ፒተር ኑዋዲኬ የፍፁም ቅጣት ምቱን በአግባቡ ተጠቅሞ አስቆጥሯል፡፡

ፍ.ቅ.ም!
70′
ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ኤፍሬም ወንድወሰን በእጁ በመንካቱ የፍጹም ቅጣት ምት ለባንክ ተሰጥቷል፡፡

ጎልልል!!! ቡና!!!!
64′ ጋቶች ፓኖም ሙሴ ገብረኪዳን ከወደቀበት በተቃራኒ መትቶ የቡናን 4ኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡

ፍቅም!!!
63′
ሳሙኤል ሳኑሚ ግብ ጠባቂውን ለማለፍ ሲሞክር በመጠለፉ የፍፁም ቅጣት ምት ለቡና ተሰጥቷል፡፡

ጎልልል!!!! ቡና!!!!!
59′ ኤልያስ በግሩም ሁኔታ በተከላካዮች መሃል ያሾለከለትን ኳስ ተጠቅሞ በምርጥ አጨራረስ የቡናን 3ኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
57′
አዲሱ ሰይፉ ወጥቶ ዳንኤል አድሃኖም ገብቷል፡፡

58′ ፒተር ኑዋዲኬ ከወንድይፍራው የነጠቀውን ኳስ በቀጥታ ሞክሮ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

53′ ጋቶች ፓኖም ከቅጣት ምት በቀጥታ የሞከረውን ኳስ ሙሴ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
51′
ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን ወጥቶ ኤፍሬመም ካሳ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! ቡና!!!!
49′ አስቻለው ግርማ ከኤልያስ ማሞ የተቀበለውን ኳስ ተረጋግቶ ተከላካዮችን በማለፍ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡ 2-0

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ባንክ
ታድዮስ ወልዴ ወጥቶ አምሃ በለጠ ገብቷል፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በቡና 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

40′ ጨዋታው ቀስ በቀስ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡

ጎልልል!!!! ቡና!!!
31′ ሳሙኤል ሳኑሚ ከጋቶች ከሳጥን ውስጥ የተቀበለውን ኳስ በጥሩ ሁኔተታ ተቆጣጥሮ ቡናን ቀዳሚ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል፡፡

28′ እያሱ ታምሩ ያሻገረውን ኳስ ሳኑሚ በቮሊ ሞክሮ ግብ ጠባቂው ሙሴ አድኖበታል፡፡ ግሩም ሙከራ!

26′ አህመድ ረሺድ ከቀኝ መስመር ያሻገረው ኳስ አቅጣጫ ቀይሮ በግቡ ቋሚ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

22′ ሳሙኤል ሳኑሚ ከግራ መስመር ገፍቶ በመግባት የሞከረው ኳስ በግቡ የቀኝ ቋሚ ለጥቂት ወጥቷል፡፡

20′ ከማዕዘን ምት የተመለሰውን ኳስ ጋቶች ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

19′ አስቻለው ግርማ ከመስመር ያጠፈውን ኳስ ቶክ ቀድሞ በመንሸራተት አውጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
16′
አዲሱ ሰይፉ ሳይጠለፍ ወድቋል በሚል የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

15′ ኢትዮጵያ ቡና በኳስ ቁጥጥር የተሻለ ቢሆንም በማጥቃት ወረዳው አደጋ መፍጠር አልቻሉም፡፡

ቢጫ ካርድ
5′
አስናቀ ሞገስ በዮናስ ገረመው ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በአስቻለው ግርማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
ቡና ከቀኝ ወደ ግራ ፣ ንግድ ባንክ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡


ጨዋታውን ኢንተርናሽናል አርቢቴር ኃይለየሱስ ባዘዘው ይመራዋል፡፡


* ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጭ በጥቁር ፤ ኢትዮጵያ ቡና ሙሉ ቡኒ መለያ ለብሰዋል፡፡


09:55 ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተው ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

09:45 ሁለቱ ቡድኖች ሰውነታቸውን አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡


09 ፡ 30 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡


የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ

99 ሀሪስን ሄሱ

13 አህመድ ረሽድ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን – 21 አስናቀ ሞገስ

9 ኤልያስ ማሞ – 25 ጋቶች ፓኖም – 19 አክሊሉ ዋለልኝ

14 እያሱ ታምሩ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ – 24 አስቻለው ግርማ


ተጠባባቂዎች

29 ዮሃንስ በዛብህ
18 ሳለአምላክ ተገኝ
4 ኤኮ ፌቨር
28. ያቡን ዊልያም
27. ዮሴፍ ዳሙዬ
17. አብዱልከሪም ሀሰን
15 አብዱልከሪም መሀመድ


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ

1 ሙሴ ገብረኪዳን

5 ቶክ ጀምስ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 12 አቤል አበበ – 27 አንተነህ ገብረክርስቶስ

18 ታዲዮስ ወልዴ

15 አዲሱ ሰይፋ – 21 ዮናስ ገረመው – 80 ቢኒያም በላይ – 2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን

19 ፒተር ንዋድኬ


ተጠባባቂዎች
22 ፋሪስ አለዋ
98 ዳንኤል አድሃኖም
32 ኤፍሬም ካሳ
6 አምሃ በለጠ
26 ጌቱ ረፌራ
44 ሳሙኤል ዮሃንስ
99 ዳንኤል ለታ

የሁለቱን ቡድኖች ወቅታዊ ውጤቶች ስንመለከት በ13ኛው ሳምንት አበበ ቢቂላ ላይ አአ ከተማን 1-0 ሲያሸንፍ ዮጵየያ ንግድ ባንክ ከ ወላይታ ቻ 2-2 አቻ መለያየቱ ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና 20 ነጥቦችን ሰብስቦ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ንግድ ባንክ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ13 ነጥቦች 11ኛ ደረጃን ይዟል።


ሠላም ውድ የሶከር ኢትዮጵያ ተከታታዮች ። በኢትዮጵያ ቡና እና ኢትጵየያ ንግድ ባንክ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ ለማድረስ ተዘጋጅተናል፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !

2 Comments

  1. It is very positive to start this kind of service in our country .keep it up and be stroung for the future.i admire you .thanks

Leave a Reply