ኢትዮጵያ ቡና 0-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ ፡ ታክቲካዊ ትንታኔ

ትላንት በ10፡00 የተካሄደው የሳምነቱ ተጠባቂ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይነት ተጠናቋል፡፡ የሶከር ኢትዮጵያው ሚልኪያስ አበራ ጨዋታውን ተመልክቶ የሚከተለውን ታክቲካዊ ትንታኔ አሰናድቷል፡፡

በትላንት ምሽቱ የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጀመርያው አጋማሽ በ3-4-3 ፎርሜሽን (ወደ 3-1-4-2 የተጫዋቾች የሜዳ ላይ አደራደር የተጠጋ) ጨዋውን የጀመረ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ የበለጠ መከላከል ላይ ያዘበለ4-2-3-1 ሙሉ የጨዋታውን ክፍለጊዜ ተጠቅሟል፡፡

(ምስል 1)

3-4-3 እና የቡና አተገባበር

በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ 3-4-3 ፎርሜሽን የመሃል ሜዳ አማካዮች ጊዜያቸውን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በማጥቃት እና በመከላከል ላይ እንዲያውሉ ያግዛል፡፡ በላይኛው የተጋጣሚ ሜዳ በከፍተኛ ፍጥነት እና የተሸለ የፊት መስመር ተሰላፊዎች ቁጥርም ተጋጣሚ ላይ ጫና መፍጠር ያስችላል፡፡ ሁለቱንም channels (በተጋጣሚ የመስመር ተከላካይ እና የመሃል ተከላካይ መካከል ያለውን ክፍተት ለመጠቀም የሚያስችል የተጫዋቾች የpositioning (ቦታን) ከመስጠቱም በተጨማሪ በነዚሁ አስፍተው ወደ መስመሩ ተጠግተው(wide forwards ) በሚሰለፉት አጥቂዎች አማካኝነት የተጋጣሚን የመስመር ተከላካዮች የፊት ለፊት የማጥቃት እንቅስቃሴ (overlapping movement) ለመከላከል ወይም አፍኖ ለመያዝ (stifle ለማድረግ) አመቺ ነው፡፡ በመካከለኛው የሜዳ ቁመት የሚያጠቃን ቡደን ለመቋቋም የሚያስችል የbackline መዘርጋት የሚያስችል በመሆኑ ሶስቱ የመሃል ተከላካዮች እጥብበው ጠንካራ የቀጥተኛ አጨዋወትን የሚተገብር ቡድን መከላከል እንዲችሉ ያግዛል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በዚህ ስርአት (የአጨዋወት ዘዴ) የራሳቸውን ስልት ተጠቅመው ጋቶች ፓኖም ከተከላካዮች ፊት በሜዳው አጋማሽ እየተንቀሳቀሰ (lateral movement) ለbackline ጥሩ የመከላከል ሽፋን ሲሰጥ ነበር፡፡ ከኤፍሬም (ከመሃከለኛው ተከላካይ ጎን) በመገኘትም ወደ መስመር ተጠግተው ሲጫወቱ የነበሩት (አህመድ እና ሚልዮን የሚፈጥሩትን) ክፈተት ለመድፈን ሞከረዋል፡፡

ከፊቱ የተሰለፉት መስኡድ ፣ ኤልያስ እና ዳዊት ይበልጥ የማጥቃት ባህርይን የተላበሱ በመሆናቸው የሚፈጥሩትን ክፍተት ሲሸፍን ተስተሏል፡፡ በመስመሮች መካከል የ10 ቁጥር ሚናን እንዲወጣ የተደረገውን አዳነን ማርክ በማድረግ የተሸለ ሲንቀሳቀስ በር፡፡ ቡና በተለይ በቀኝ መስመር የwidth ችግር ይስተዋልበት ነበር፡፡ በመጀመርያዎቹ 13 ደቂቃዎች ውስጥም የቡድኑ እንቅስቃሴ እና የተጫዋቾች የሚና አተገባበር ከ3-4-3 ይልቅ ወደ 3-1-4-2 ያይ ነበር፡፡ ይህም ሁለቱ አጥቂዎች በተጋጣሚው ሳጥን አካበቢ በአንድ የአግድሞሽ መስመር ላይ ከመገኘታቸውና አስቻለውም ከአጥቂዎቹ መስመር ይልቅ ወደ አማካኞቹ ቀርቦ ከመገኘቱ ጋር የተያያዘ ይመስለል፡፡ አስቻለው በቡና የማጥቃት አጨዋወት attacking phase ወደ ፊት ሲሔድ የቀኝ መስመሩ ክፍት ሲሆን ይታይ ነበር፡፡ ነገር ግን በጊዮርጊስ ግራ አጥቂ አማካኝነት የተሰለፈው ዳዋ ሁቴሳ ያንን ሰፊ ክፍተት ሊጠቀምበት አልቻለም፡፡

በእርግጥ የቡና የ3 ተከላካይ ክፍል (back 3) ኳሷን ያማከለ የመከላከል ስልት (ball oriented movement) በማድረግ እና በመካከል ያለውን የአግድሞሽ ክፍተት በማጥበብ (ይበልጥ compact በመሆን) በመካከላቸው ያለውን ክፈተት (channels) ሲያጠቡ ተስተውለዋል፡፡ ተጋጣሚያቸው በፊት መስመሩ ላይ አንድ አጥቂ ብቻ ማሰለፉም የተከላካይ ክፍሉ ያን ያህል ሲፈተን አልታየም፡፡

በመከላከል አጨዋወት አልፎ አልፎ ቢንያም ወደ መስመር እየወጣ እና ወደ ኋላ እየተመለሰ ሲያግዝ ታይቷል፡፡ በ13ኛው ደቂቃ አስቻለው ወደ ግራ መስመር ከሄደ በኋላ መስኡድ ወደ ቀኝ መጥቶ በ14ኛው ደቂ በአግዳሚው ላይ ያለፈች የግብ ሙከራ ማድረግ ችሏል፡፡ በጨዋtaው የመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች በጊዮርጊስ መስመር አሉላ እና በኃይሉ ጥሩ የመስመር ጥምረት ፈጥረው ፈጣን የመስመር ሽግግሮች (flank transition) ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ አሉላ በመጠኑ የመስመር የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ለማድረግ ሞክሯል፡፡ በኃይሉም ከ15ኛው ደቂቃ በኋላ ከዳዋ ጋር የቦታ ለውጥ አድርጓል፡፡ በ16ኛው ደቂቃ ላይም ተስፋዬ በረጅሙ የላከውን ኳስ (መሬት ሳትነካ) በቮሊ ወደ ግብ የሞከራት ለዚህ ማመልከቻ ነበረች፡፡ ጊዮርጊስ ከቆሙ ኳሶች (ከማእዘን እና ከቅጣ ምቶች) የሳላዲንን የጭንቅላት ኳሶች ለመጠቀም ሲሞክሩ ጥሩ ነበሩ፡፡ በተለይ በfarpost የሚደርሱት ኳሶች በሙሉ ሳላዲንን ያለሙ ይመስሉ ነበር፡፡ የበኃይሉ ወደ ግራ መስመር መምጣት አዳነን የበለጠ እንዲንቀሳቀስ አድርጎታል፡፡ ምንተስኖት በሜዳው ቁመት ወደፊት እየተጠጋ አዳነን በማጥቃ ክልሉ ለማገዝ ቢሞክርም ይበልጥ መከላከል ላይ አመዝኖ ታይቷል፡፡ ይህም በጊዮርጊስ አጥቂ አማካይ መካከል ሰፊ ክፍተት እንዲኖር አድርጓል፡፡ዳዋ እና በኃይሉም ይበልጥ ወደ መስመር አዘንብለው በመጫወታቸው ቡናዎች በመሃል ሜዳ ላይ መጠነኛ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት መውሰድ አስችሏቸዋል፡፡

(ምስል 2)

2

ሁለተኛው አጋማሽ

ቅዱስ ጊዮርጊሶች የአንዋርን ታክቲካዊ ለውጥ የተጠቀሙበት መንገድ

ከእረፍት መልስ ሁለቱም ቡድኖች የተጫዋቾች ለውጥ አድርጎ ገብቷል፡፡ ጊዮርጊስ በጉዳት ምክንያት አሉላን በአለማየው ሲተካ ቡናዎች ደግሞ ሮቤልን በአስቻለው ቀይረው ቀርበዋል፡፡

የአሰልጣኝ አንዋር የተጫዋች ለውጥ በቡድን ቅርፅ ላይ ልዩነት ፈጥሯል፡፡ አህመድ የቀኝ መስመር ፉልባክ ፣ ሮቤልን በግራ የመስመር ተከላካይ አሰልፈውታል፡፡ ይህም የቡናን የተከላካይ መስመር ከ3 ተከላካይ ወደ 4 ተከላካይ እንዲለወጥ አድረጎታል፡፡ ጋቶች ለተከላካይ መስመሩ ሽፋን ሲሰጥ በማጥቃት አማካይነት ደግሞ መስኡድ በግራ ኤልያስ በመሃል (በ10 ቁጥር ሚና) ፣ ዳዊት ደግሞ በቀኝ ሆኖ ተሰልፏል፡፡ ሁለቱ አጥቂዎች ቢንያም እና ሻኪሩም በሳጥኑ ክልል በአግድሞሽ መስመር በአንድ ላይ መጫወት ጀመሩ፡፡ ይህም የቡድኑን ቅርፅ ወደ 4-1-3-2 ቀይሮታል፡፡ ቀድሞ የነበራቸውን የመሃል ሜዳ ተጫዋቾች የቁጥር መጠን የቀነሰው የሲስተም ለውጥ ቡድኑን ይበልጥ ስፋት (width) አሳጥቶታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊሶችም በተለይ በግራ መስመር የነበረውን የቡና width ችግር በሚገባ ተጠቅመው ሁለቱንም የማሸነፍያ ግቦች ከዚሁ መስር ማግኘት ችለዋል፡፡ የመስኡድ እና ዳዊት 4-1-3-2 እንደ shutlerrs የመስመር አማካኞች ከመጫወት ይልቅ ወደ መሃለኛው ሜዳ ስለሚገቡ ለጊዮርጊሶች የተሸለክፈተትን እና ነፃነትን መስጠት ጀመሩ፡፡ 4-1-3-2 ቡድኖች በብዛት የተጋጣሚን ሜዳ ለመቆጣጠር በሚፈልጉበት ስልት የሚጠቀሙበት ሆቢንም በጥሩ የመከላከል አደረጃጀት የቀረበውን ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚፈትን እንቅስቃሴ ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ከእረፍት በፊት የታቀደበት በማይመስል ነገር ግን ሲጠቅማቸው በነበረው የመሃል አማካዮች የrevolving movement የኤልያስ ፣ ዳዊት እና መስኡድ ከቅርፅ ውጪ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የበለጠ መሃል ሜዳ ላይ ብልጫ እንዲኖራቸው አድርጎ ነበር፡፡ ፈረሰኞቹ በሁለተኛው አጋማሽ ተስፋዬ እና ምንተስኖት በመጠኑ ወደ ፊት ማስጠጋታቸው እነ ዳዊትን ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ አድርጓል፡፡ ቀድሞ በማጥቃት እንቅስቃሴ ( overlapping movement ) ቀጥተኛ የመስር የፊት ለፊት ተደጋጋሚ ሩጫዎችን ሲያደርግ የሚስተዋለው ዘካርያስ ቱጂ የበለጠ የመከላከል ስራ ላይ ማተኮሩ ለጊዮርጊስ የተረጋጋ እና የተደራጀ (stable and organized back-line) የመከላከል መስመር እንዲኖረው አግዞታል፡፡

(ምስል 3)

3

በኃይሉ እና ተፅእኖው

በኃይሉ አሰፋ ድል መሰረት ነበር፡፡ ለቡድኑ አሸናፊነት አይነተኛ አስተዋፅኦ አበርካች ቱሳ ነበር፡፡ በሁለቱም መስሮች ከዳዋ ጋር እየተቀያየረ ለጊዮርጊስ የማጥቃት አጨዋወት ከፍተኛ እገዛ ሲያበረክት ተስተውሏል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ከመስመር ወደ ውስጥ (cut inside) እየገባ ፣ በሜዳ አግድሞሽ እየተንቀሳቀሰ እና ከቡና የመስመር ተከላካዮች ጀርባ እየተገኘ የቡድኑን የማጥቃት ማእዘን (attacking angles) ለማስፋት ጥሯል፡፡ በተጨማሪም ወደኋላ እየተመለሰ ለቡድን አጋሮቹ የመቀባበያ አማራጮችን (passing lane options) ሲፈጥር ታይቷል፡፡ በ1ኛው ደቂቃ ላይም ከግራ መስመር በረጅሙ ለአጥቂው ብሪያን ኡሞኒ የላካት ኳስ በግንባር ተገጭታ ግብ ስትሆን ኳሷን ያሻገረበት መንገድ እጅግ ወሳኝ ነበር፡፡ ከ3 ደቂቃች በኋላም ከዚሁ መስመር ተነስቶ ራሱ ያስቆጠራት ግብ የቡድኑን የአሸናፊነት ስነልቡና ከፍ ያደረገችና የቡናዎችን ተስፋ ያደበዘዘች ነበረች፡፡ ብራቮ ቱሳ!

(ምስል 4)

4

 

*ማስተካከያ ፡ በመጨረሻዎቹ 2 ምስሎች ላይ የቡና አሰላለፍ 3-1-4-2 ሳይሆን 4-1-3-2 ነው፡፡

ያጋሩ