ፍሬው ሰለሞን ይቅርታ ጠይቋል

ሀዋሳ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ በተለያዩበት የ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በዮናታን ከበደ ተቀይሮ ሲወጣ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ላይ ያልተገባ ባህርይ ያሳየው ፍሬው ሰለሞን በይፋ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

“በወቅቱ የሰራሁት ስህተት እጅግ አሳፋሪ እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡ ይህ ያልተገባ ባህሪ ነው፡፡ ስለዚህ አሰልጣኝ ውበቱን ፣ የአሰልጣኞች ቡድን አባላትን ፣ ደጋፊዎችን ፣  የከክለቡ ቦርድ አባላት እና ሚዲያውን እጅግ ይቅርታ እጠይቃለው፡፡ ” ያለው ፍሬው ሰለሞን ችግሮች በመፈታታቸው ወደ ውጤታማነት እንደሚመለሱ ተናግሯል፡፡

” አሁን ችግራችንን በመነጋገር ፈትተናል፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ከቡድን አጋሮቼ ጋር ጥሩ ውጤት ለማምጣት እንሰራለን፡፡ ከውጤት ቀውስ በመውጣት ክለቡን የተሻለ እናደርገዋለን፡፡ ” ብሏል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በሊጉ 14ኛ ሳምንት ዛሬ በሜዳው ጅማ አባ ቡናን ያስተናግዳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *