ሀዋሳ ከተማ ከ ጅማ አባ ቡና | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTሀዋሳ ከተማ 2-1 ጅማ አባ ቡና

59′ ፍሬው ሰለሞን (P)፣ 67′ ጋዲሳ መብራቴ || 45+1′ አሜ መሐመድ


ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

90+3′ የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ ከተማ

ደስታ ዮሀንስ ወጥቶ አዲስ አለም ተስፋዬ ገብቷል።

90+2′ ጃኮ አረፋት ጋዲሳ በረጅሙ የሰጠውን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ መትቶ ኳሱ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ነክታ ወጥቷል። 

90′ ተጨማሪ ሰዐት – 4 ደቂቃ

88′ የተጫዋች ለውጥ ጅማ

መሀመድ ናስር ወጥቶ ቴዎድሮስ ታፈሰ ገብቷል።

86′ ዳንኤል በጥሩ ሁኔታ የሰጠውን ኳስ ጃኮ አረፋት በግንባሩ ገጭቶ በቀኝ ቋሚ በኩል ወጥቶበታል።

83′ የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ ከተማ

ታፈሰ ሰለሞን ወጥቶ አስጨናቂ ሉቃስ ገብቷል።

77′ ደስታ ዩሀንስ ከመስመር ሰንጥቆ ገብቶ ያቀበለውን ኳስ ኤፍሬም ዘካርያስ መጠቀም አልቻለም።

71′ ታፈሰ ሰለሞን ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ዳንኤል ወደ ግብ ሞክሮ ሙላት በቀላሉ ይዞበታል።

67′ ጎል!!!

ጋዲሳ መብራቴ ኤፍሬም በረጅሙ ያሻገረውን ኳስ በግምት 25 ሜትር ርቀት መትቶ በማስቆጠር ሀዋሳን መሪ አድርጓል።

63′ የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ ከተማ

ዮናታን ከበደ ወጥቶ ኤፍሬም ዘካሪያስ ገብቷል።

59′ ጎል!!!!

ፍሬው ሰለሞን የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት በአግባቡ ተጠቅሞ ሀዋሳ ከተማን አቻ አድርጓል።

58′ ደስታ ዮሀንስ ላይ ጥፋት በመፈፀሙ ሀዋሳ ፍፁም ቅጣት ምት አገኘ።

57′ የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና

ዳዊት ተፈራ ወጥቶ ሀይደር ሸረፋ ገብቷል።

47′ ፍሬው ሰለሞን የጅማ ግብ ክልል ውስጥ አስመስለህ ወድቀሀል በሚል ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።

46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ በሀዋሳ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል።


ጅማ አባ ቡና በጭማሪ ሰዓት ባስቆጠረው ግብ 1-0 እየመራ የመጀመሪያውን የጨዋታ አጋማሽ አጠናቋል።


45+1′ ጎል!!!!

መሐመድ ናስር ከማዕዘን ያሻማውን ኳስ አሜ መሐመድ የሀዋሳ ተከላካዮችን ስህተት ተጠቅሞ ወደግብ በመቀየር ጅማን መሪ አድርጓል።

45′ ተጨማሪ ሰዓት – 1 ደቂቃ

40′ የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና

ሂደር ሙስጠፋ ወጥቶ ታደለ ምህረቴ ገብቷል።

38′ ጋዲሳ መብራቴ ተደጋጋሚ ኳሶችን ከርቀት በመምታት ግብ ጠባቂው ሙላትን እየፈተነ ይገኛል፡፡

32′ ሀዋሳ ከተማ ወደ ግብ በመድረስ ጅማ አባ ቡና በመከላከሉ የተሻለ እንቅስቃሴ እያሳዩ ነው።

26′ ጃኮ አረፋት ከርቀት የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሙላት አውጥቶታል።

23′ ዳንኤል ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ደስታ ዩሀንስ በግንባር ገጭቶ ሀዋሳን መሪ የሚያደርግ ግብ አስቆጠረ ሲባል ኳሱ የግቡን ቋሚ ለትሞ ወጥቷል።

21′ አሜ መሀመድ በፈጣን እንቅስቃሴ እየገፋ ገብቶ ወደ ግብ ቢመታም ከግቡ ጠርዝ ላይ መላኩ ተደርቦ አወጣበት።

18′ ፍሬው በግሩም ሁኔታ መሀል ለመሀል ያሾለከውን ኳስ ዮናታን ከበደ ቢያገኘውም ሊጠቀምበት አልቻለም።

12′ ደስታ ዮሀንሰ ከጋዲሳ ጋር በአንድ ሁለት ቅብብል ያሻገረውን ኳስ አረፋት በግንባሩ ገጭቶ ሙላት አለማየው ይዞታል፡፡

9′ ዳንኤል ደርቤ በመስመር እየገፋ ገብቶ የሰጠውን ኳስ ጃኮ አረፋት ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በጅማ አባ ቡና አማካኝነት ተጀመረ፡፡


ኢ/ር ዳኛ ዘካሪያስ ግርማ የጨዋታው ዋና ዳኛ ሲሆኑ ረዳት ፌድራል ዳኛ አሸብር ታፈሰ እና ላቀው ደጀኔ እንዲሁም ፌድራል ዳኛ አብረሀም ኮይራ በአራተኛ ዳኝነት በጋራ ጫወታውን ይመሩታል፡፡​ የጨዋታው ኮሚሽነር አቶ መኮንን አሰረስ ናቸው።


8:36 ደጋፊው ከሌላ ጊዜ በተሻለ ሀዋሳን ለመደገፍ ገብቷል፡፡

09:30 ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ

1 ሶሆሆ ሜንሳ

7 ዳንኤል ደርቤ – 13 መሳይ ጳውሎስ – 22 መላኩ ወልዴ – 12 ደስታ ዮሀንስ

5 ታፈሰ ሰለሞን – 24 ኃይማኖት ወርቁ 10 ፍሬው ሰለሞን

11 ጋዲሳ መብራቴ – 15 ጃኮ አራፋት – 16 ዮናታን ከበደ

ተጠባባቂዎች

30 አላዛር መርኔ

4 አስጨናቂ ሉቃስ

9 እስራኤል እሸቱ

6 አዲስአለም ተስፋዬ

27 ፍርዳወቅ ሲሳይ

3 ኤፍሬም ዘካርያስ

19 ዮሃንስ ሰገቦ


የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ

1 ሙላቱ አለማየሁ

5 ጀሚል ያዕቆብ – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 21 በኃይሉ በለጠ – 14 ሂድር ሙስጠፋ

11 ዳዊት ተፈራ – 27 ክርቶፈር ንታንቢ – 18 ኃይለየሱስ ብርሃኑ – 20 ኪዳኔ አሰፋ

9 አሜ መሀመድ – 25 መሀመድ ናስር

ተጠባባቂዎች

22 በሽር ደሊል

7 በድሉ መርዕድ

4 ሀይደር ሸረፋ

6 ታደለ ምህረቴ

8 ሱራፌል አወል

10 ቴዎድሮስ ታደሰ

19 ልደቱ ግታቸው

Leave a Reply