ድሬዳዋ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTድሬዳዋ ከተማ 1-0 ፋሲል ከተማ

1′ ሀብታሙ ወልዴ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

ቢጫ ድሬደዋ ከተማ
88″ ሳምሶን አሰፋ ሰአት በማባከን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ ድሬደዋ ከተማ
81″ አሳምነው አንጀሎ ወጥቶ ረመዳን ናስር ገብቷል

የተጨዋች ለውጥ ፈሲል ከነማ
79″ ናትናኤል ጋንቹላ ወቶ ኤርምያስ በለጠ ወቷል

77″ ድሬደዋ ከተማ ውጤት ለማስጠበቅ አፄዎቹ የአቻነት ጎል ፍለጋ ጠንካራ የሆነ የጨዋታ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል፡፡

የተጨዋች ለውጥ ድሬደዋ ከተማ
70′ ፍቃዱ ወርቁ ገብቷል በረከት ይስሐቅ ወጥቷል

69′ አፄዎቹ የአቻነት ጎል ፍለጋ ጥረት ቢያደርጉም ጠንካራውን የድሬደዋ ከተማ ተከላካዮችን ሰብረው መግባት አልቻሉም፡፡

የተጨዋች ለውጥ ድሬደዋ ከተማ
67′ አልሳሪ አልምሀዲ ገብቶ ሚካኤል ለማ ወጥቷል

የተጨዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
62′ ሙሉቀን ታሪኩ ገብቶ ኤዶም ወጥቷል

60′ ጨዋታው ማራኪ እንቅስቃሴ እየታየበት አይገኝም፡፡ በተደጋጋሚ በመሚነፋ ፊሽካም ጨዋታው እየተቆራረጠ ይገኛል፡፡

53′ ፋሲል ከተማዎች በተደጋጋሚ ወደ ጎል ለመቅረብ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ፋሲል
47′ ኤፍሬም አለሙ ገብቶ ሰለሞን ገ/መድህን ወጥቷል፡፡

ተጀመረ !
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት !
የመጀመርያው አጋማሽ በድሬደዋ ከተማ 1 – 0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

44′ አሳምነው አንጀሎ ያሻማውን በረከት ይስሐቅ በግራ እግሩ መቶ ለጥቂት ወጣበት፡፡

ቢጫ! ፋሲል
41′ ይስሐቅ መኩርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

34′ ጨዋታው የሀይል እንቅስቃሴ እየበዛበት በመምጣቱ ምክንያት በዳኛው ፊሽካ እየተቆራረጠ ይገኛል፡፡

ቢጫ ካርድ! ድሬዳዋ
32′ ኄኖክ አዱኛ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

28′ በከረከት ከአንድ ሁለት ቅብብል በኋላ ከሳጥን ውጭ የመታው ኳስ ለጥቂት በግቡ ጠርዝ ወጥቷል፡፡

23′ አብዱራህማን ሙባረክ የተከላካዮችን ስህተት ተጠቅሞ የመታውን ኳስ ሳምሶን አሰፋ በሚገርም ሁኔታ አዳነበት፡፡

21′ ሄኖክ ገመቴሳ ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ኤዶም በነፃ አቋቋም ላይ ቢገኝም ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

18′ ጨዋታው በመጀመርያዎቹ 10 ደቂቃዎች በነበረው ፍጥነት መቀጠል ሳይችል እየተቀዛቀዘ ይገኛል፡፡

12′ በመጀመርያው ደቂቃ በተቆጠረባቸው ጎል ተደናግጠው የነበሩት አፄዎች አሁን ተረጋግተው ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

5′ ጨዋታው በሚገርም ሁኔታ በፈጣን እንቅስቃሴ ተጋግሎ ቀጥሏል፡፡

ጎልልል!!! ድሬደዋ ከተማ!!!
1′ ሀብታሙ ወልዴ ገና በመጀመርያው ደቂቃ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው በድሬደዋ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

ድሬደዋ ነጭ ማልያ በጥቁር ቁምጣ ፋሲል ከተማ ነጭ በቀይ ስትራይፕ ለብሰው ገብተዋል፡፡

በዕለቱ ኮሚሽነር ዳንኤል ፈቀደ እየተመሩ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ በመግባት ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛል፡፡

ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የፋሲል ከተማ ደጋፊዎች በድሬደዋ ስቴዲዮም በመገኝት ክለባቸውን እያበረታቱ ይገኛሉ፡፡

​09:50 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ሰውነታቸውን አፍታተው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

09:25 የሁለቱም ቡድኖች ተጨዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡

የዕለቱን ጨዋታ ፌዴራል ዳኛ ዳንኤል ግርማይ ይመሩታል

ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት ዋላችሁልን የሶከር ኢትዮዽያ ተከታታዮች፡፡ በኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛው ሳምንት ጨዋታ ድሬደዋ ላይ በድሬደዋ ከተማ እና በፋሲል ከተማ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በቀጥታ የፁሁፍ ስርጭት እንድትከታተሉን እንጋብዛለን፡፡

መልካም ጊዜ ከሶከር ኢትዮዽያ ጋር  !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *