ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዲስ አበባ ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTቅዱስ ጊዮርጊስ 1-1 አአ ከተማ

89′ ምንተስኖት አዳነ 40′ ኃይሌ እሸቱ


ተጠናቀቀ!

ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ 4

ጎልልል!!! ጊዮርጊስ!!!
89′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ተጠቅሞ ምነንተስኖት አዳነ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡ 1-1
የተጫዋች ለውጥ – አአ ከተማ
87′ ዳዊት ማሞ (ጉዳት) ወጥቶ አማረ በቀለ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
86′ ደረጄ አለሙ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

85′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ምንተስኖት ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አአ ከተማ
82′ ፍቃዱ አለሙ ወጥቶ ምንየያምር ጵጥሮስ ገብቷል፡፡

79′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ምንተስኖት በግንባሩ ገጭቶ እነየው ከግቡ መስመር አውጥቶታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
79′ መሃሪ መና ወጥቶ አበባው ቡታቆ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አአ ከተማ
75′ ከነአን ማርክነህ ወጥቶ ፀጋ አለማየሁ ገብቷል፡፡

73′ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጫና እየፈጠረ ቢገኝም የአአ ከተማን የሚፈትን እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻሉም፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
62′ አቡበከር ሳኒ ወጥቶ ሳላዲን ሰኢድ ገብቷል፡፡

55′ ሙሃጅር መኪ በድጋሚ አክርሮ የመታውን ኳስ ፍሬው አውጥቶታል፡፡ ግሩም ሙከራ!

53′ ሙሃጅር ከግራ መስመር የሞከረውን ኳስ ፍሬው ይዞበታል፡፡

51′ አቡበከር ሳኒ ከሳጥኑ ጠርዝ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

50′ ሙሃጅር መኪ ተንሸራቶ የሞከረውን ኳስ ፍሬው ጌታሁን ይዞበታል፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ!

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ጊዮርጊስ
ዘካርያስ ቱጂ ወጥቶ በሃይሉ አሰፋ ገብቷል፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በአአ ከተማ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

ጎልልል!!! አአ ከተማ!
40′ ኃይሌ እሸቱ ከፍቃዱ የተቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ አአ ከተማን ቀዳሚ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል፡፡

33′ ዘካርያስ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አቡበከር ሳኒ ሞክሮ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

31′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ምንተስኖት ሞክር በቀላሉ ተይዞበታል፡፡

25′ ጨዋታው የግብ ሙከራዎች እየታዩበት አይደለም፡፡

17′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች በፈጣን እንቅስቃሴ አደጋ ለመፍጠር እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡

9′ ከዘካርያስ ቱጂ የተሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ በግምባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

7′ እንየው ካሳሁን የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በአአ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

09:45 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበኻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

1 ፍሬው ጌታሁን

25 አንዳርጋለው ይላቅ -12 ደጉ ደበበ 23 ምንተስኖት አዳነ – 3 መሃሪ መና

24 ያስር ሙገርዋ – 26 ናትናኤል ዘለቀ

18 አቡበከር ሳኒ – 10 ራምኬል ሎክ – 20 ዘካርያስ ቱጂ

19 አዳነ ግርማ
ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
2 ፍሬዘር ካሳ
4 አበባው ቡታቆ
15 አስቻለው ታመነ
13 ሳላዲን በርጊቾ
7 ሳላዲን ሰኢድ
16 በሃይሉ አሰፋ

የአዲስ አበባ ከተማ አሰላለፍ

98 ደረጄ አለሙ

81 አለማየሁ ሙለታ – 6 ጊት ጋትኮች 20 ሰይፈ መገርሳ – 2 እንየው ካሳሁን

13 ዘሪሁን ብርሃኑ
50 ከነአን ማርክነህ – 30 ሙሃጅር መኪ – 40 ዳዊት ማሞ

24 ፍቃዱ አለሙ – 8 ኃይሌ እሸቱ

ተጠባባቂዎች

1 ተክለማርያም ሻንቆ

7 ምንያምር ጵጥሮስ
70 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ
77 አማረ በቀለ
83 ጸጋ አለማየሁ
60 እሱባለው ሙሉጌታ
80 አዳነ በላይነህ

93 አዳነ በላይነህ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት ዋላችሁልን የሶከር ኢትዮዽያ ተከታታዮች፡፡ በኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛው ሳምንት አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና አአ ከተማ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በቀጥታ የፁሁፍ ስርጭት እንድትከታተሉን እንጋብዛለን፡፡

መልካም ጊዜ ከሶከር ኢትዮዽያ ጋር  !!

Leave a Reply