ሀዋሳ ከተማ 2-1 ጅማ አባ ቡና | የአሰልጣኞች አስተያየት

ውበቱ አባተ – ሀዋሳ ከተማ

ስለ ጨዋታው

ከረጅም ጨዋታ በኃላ ነው ያሸነፍነው፡፡ እኛ እስካሁንም በአሳማኝ ሁኔታ ሳይሆን በጥቃቅን ስህተት ነበር እያጣን የነበረው፡፡

በጨዋታው ተደጋጋሚ ግብ የማግባት እድሎችን ፈጥረናል፡፡ ኳስ እግራችን ስር ለረጅም ጊዜ ይቆይ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ግብ ማስቆጠር እንችል ነበር፡፡ እነሱ ግን ሁለት እድሎች ፈጥረው አንዱን አስቆጥረዋል፡፡ እኛ ደግሞ ተደጋጋሚ ሙከራ ፈጥረናል፡፡ ጋዲሳ ካገባም በኃላ ያለቀላቸውን ኳስ አምክነናል፡፡ ነገር ግን ከሌላ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ተንቀሳቅሰናል፡፡ ጥረታችን ሁሉ በመጨረሻ ተሳክቷል፡፡

ወደ ድል መመለስ…

ማሸነፋችን አንድ ነገር አሳይቶናል፡፡ ስልጠናችን ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደዚህ በውጤት ሲታጀብ ደግሞ ደስ ይላል፡፡ ከውስጣችን የነበረንን ሁሉ ጥላቻ አውጥተን ነበር የቀረብነው፡፡

ቀጣይ..

ከዚህ በኃላ በሚኖሩ ጨዋታወች ላይ ተመሳሳይ ነገሮችን እንተገብራለን፡፡  በቀጣይ ጨዋታዎች የራቁንን ለመጠጋት ማሸነፍ ይጠበቅብናል፡፡

ገብረመድህን ኃይሌ – ጅማ አባ ቡና

ስለ ጨዋታው

ከሜዳችን ውጭ ነው የተጫወትነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከተደጋጋሚ ሽንፈት ነው የመጣነው፡፡ ከሜዳ ውጪ ቢከብድም ቀድመን ግብ አስቆጥረን ነበር ፤ በመልሶ ማጥቃት ያሰብነውን እቅድ ባናሳካም ኳስ ስለሆነ ምንም ምክንያት መፍጠር አያስፈልግም፡፡ ከአሁን በኋላ ወደ አሸናፊነት ማሸነፍ ግድ ነው፡፡

የዳዊት ጉዳት

የዳዊት መውጣት አልጎዳንም ምንም እንኳ ፈጣሪ ተጫዋች ቢሆንም እንጀ ቡድን በማጥቃትም ፣ በመከላከልም ጥሩ አልነበርንም፡፡ ስለሆነም የዳዊት መጎዳት ለኛ ምክንያት አይሆንም፡፡ ውጤቱን ሊቀይር የቻለው የኛ ደካማ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ”

ጫና…

ሁለት ጨዋታ መሸነፍ እኔን ጫና ውስጥ አይከተኝም፡፡ እግርኳሱን በደንብ አውቀዋለው ፤ ይህ ሽንፈት እንደሚያጋጥም ይታወቃል፡፡ ለኔ በጅማ አባ ቡና ገና ሁለተኛ ጨዋታዬ ነው፡፡ ቡድኑ በሽግግር ላይ እንደመሆኑ የተወሰነ ችግሮችን አርመን በቀጣይ እንቀርባለን፡፡

Leave a Reply