​በኢትዮጵያ ዋንጫ [ጥሎ ማለፍ] የሚሳተፉ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ዋንጫ [ጥሎማለፍ] የ2009 የውድድር ዘመን በመጪው የካቲት 11 ይጀመራል፡፡ ከ2001 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከፕሪምየር ሊግ በታች የሚገኙ ክለቦችን የሚያሳትፈው የዘንድሮው ውድድር ላይ የሚካፈሉ የከፍተኛ ሊግ ቡድኖችም ታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ32 የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቢያቀርብም ክለቦቹ ዝግጁ ባለመሆናቸው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ 5 ክለቦች ብቻ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በዘንድሮው ውድድር ላይ እንደሚካፈሉ ያስታወቁት ክለቦች አራዳ ክፍለከተማ ፣ አክሱም ከተማ ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ ፣ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት እና ፌዴራል ፖሊስ ናቸው፡፡

21 ክለቦች የሚሳተፉበት ውድድር እጣ ማውጣት ስነስርአት እና ደንብ የካቲት 7 ቀን 2009 ሶዶ ከተማ ላይ ሲከናወን ሁሉም ጨዋታዎች አዲስ አበባ ላይ እንደሚደረጉ ታውቋል፡፡

Leave a Reply