የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ትልቅ ግምት በተሰጠው የኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት ጨዋታ ነገ ይጠናቀቃል፡፡
የደደቢቱን የመጋቢት 9 ድል ጨምሮ ያለፉትን 6 ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች በድል ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና ከተከታዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላለመራቅ ብርቱ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡ ከተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ በቅርቡ ወደ አሸናፊነት የተመለሱት ደደቢቶችም በአሸናፊነት ለመቀጠል ይህ ጨዋታ አስፈላጊያቸው ነው፡፡
በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮጵያ ቡና ነገ ድል ከቀናው ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለውን የ11 ነጥብ ልዩነት ወደ 8 ሲያጠብ ደደቢት ካሸነፈ በ24 ነጥቦች 3ኛ ደረጃን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግብ ልዩነቶች በመብለጥ ይረከባል፡፡
ኤፍሬም አሻሞ ከ ስዩም ተስፋዬ
ሁለቱም ወቅታዊ አቋማቸው ድንቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው የመስመር አጥቂ በተከታታይ ግብ እያስቆጠረ ሲሆን ስዩም ተስፋዬም ከቅርብ ጊዜ ደካማ አቋሙ አገግሞ በድንቅ ብቃት ላይ ይገኛል፡፡ ከሐረር ቢራ ጋር በተደረገው ጨዋታ በጉዳት ተቀይሮ ከሜዳ የወጣው ኤፍሬም አሻሞ ለነገው ጨዋታ የማይደርስ ከሆነ ለኢትዮጵያ ቡና ጨዋታውን አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ በመጀመርያው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመስመር ላይ የተመለከትነውን ጥሩ ፍልሚያ በድጋሚ ላንመለከተውም እንችላለን፡፡
የእስካሁን ግንኙነታቸው ምን ያሳየናል?
በአጠቃላይ ደደቢት ኢትዮጵያ ቡና ላይ የበላይነት አለው፡፡ በሊጉ እስካሁን 9 ጊዜ ተገናኝተው ደደቢት በ6ቱ ድል ሲቀናው ኢትዮጵያ ቡና ያሸነፈው ሶስቱን ብቻ ነው፡፡ ውድድሮች ወደ ወሳኝ ምእራፍ በሚሸጋገሩበት ሁለተኛው ዙር ሰማያዊው ጦር ከ4 አጋጣሚዎች በ3ቱ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ አቋም ካየነው ከ3 ሳምንት በፊት ኢትዮጵያ ቡና ሲያሸንፍ የቅርብ ጊዜ ጥሩ አቋምም አለው፡፡
እንዴት ሊገቡ ይችላሉ?
ሁለቱም ቡድኖች የተለመደ (ደደቢት 4-2-3-1 ፤ ኢትዮጵያ ቡና 4-3-3) አሰላለፋቸውን ቀይረው የመግባት ልምድ የላቸውም፡፡ ነገር ግን በተጫዋቾች ጉዳት ምክንያት አሰልጣኞቹ የሚና ሽግሽግ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጋብሬል ሻይቡ ካልተሰለፈ ወላይታ ድቻን በረቱበት ግጥሚያ በጥልቀት ወደ ኋላ ገብቶ የተጫወተው ታደለ መንገሻ በጋብሬል ቦታ ሊሰለፍ ይችላል፡፡ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው ሄኖክ ኢሳያስ ከ ሽመክት ጉግሳ እና መስፍን ኪዳኔ ጋር በጥምረት ከሁለቱ አማካዮአች ጋር ይሰለፋሉ፡፡
በኢትዮጵያ ቡና በኩል እንደከዚህ ቀደም ጥቂት ጨዋታዎችዳዊት እስጢፋኖስን በሰለሞን ገ/መድህን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የእርስ በእርስ ግንኙነቶች
ተገናኙ – 9
ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ – 3 (13 ግብ)
አቻ – 0
ደደቢት አሸነፈ – 6 (20 ግቦች)
{jcomments on}