ኬንያ 2018 | ኢትዮጵያ የቻን ማጣሪያ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች

ኬንያ በ2018 ለምታስተናግደው የአፍሪካ ሃገራት ዋንጫ (ቻን) የማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል ካፍ ይፋ አድርጓል፡፡ በ2014 እና 2016 ቻን ላይ ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በማጣሪያው ምስራቅ እና መካከለኛው ዞን ላይ ተኳቷል፡፡

የሁለት ዙር ማጣሪያ ባለበት ዞኑ ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ማጣሪያ ከጅቡቲ ጋር ተደልድላለች፡፡ በእግርኳሱ እምብዛም የማትታወቀው ጅቡቲ በአፍሪካ ዋንጫ ይሁን በቻን ወድድሮች ላይ ተሳትፋ አታውቅም፡፡ ኢትዮጵያ ጅቡቲ ላይ በእርስ በእርስ ግንኙነት የበላይነት መያዟ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ግምቱን ያጠናክርላታል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታ ጅቡቲ ላይ ከሃምሌ 7-9 2009 ባሉት ቀናት ሲደረግ የመልሱ ጨዋታ ከሳምንት በኃላ ከሃምሌ 14-16 ባሉት ቀናት እንዲደረግ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡

የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ አሸናፊ በመጨረሻው የማጣሪያ ዙር ከብሩንዲ እና ሱዳን አሸናፊ ጋር ይጫወታል፡፡ የመጀመሪያው ጨዋታ ከነሃሴ 5-7 ባሉት ቀናት ሲደረግ የመልስ ጨዋታው ከ15-17 ባሉት ቀናት ይደረጋል፡፡ ኢትዮጵያ በ2014 ቻን ሩዋንዳን በመለያ ምት በማሸነፍ ስታልፍ በ2016ቱ ደግሞ ኬንያን 2-0 እንዲሁም ብሩንዲን 3-2 በሆነ የአጠቃላይ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቻን ማምራት መቻሏ የታወሳል፡፡

ሙሉ የምስራቅ እና መካከለኛ አፍሪካ ዞን ድልድሉ ይህን ይመስላል

የመጀመሪያ ዙር

የሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን አሸናፊ ከ ዩጋንዳ

ታንዛኒያ ከ ሩዋንዳ

ጅቡቲ ከ ኢትዮጵያ

ብሩንዲ ከ ሱዳን 

ሁለተኛ ዙር

ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን/ ዩጋንዳ አሸናፊ ከ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ አሸናፊ

የጅቡቲ እና ኢትዮጵያ አሸናፊ ከ ብሩንዲ እና ሱዳን አሸናፊ

Leave a Reply