አዲስ አበባ ከተማ ከ ወልድያ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTአአ ከተማ 1-1 ወልድያ 

58′ ዳዊት ማሞ 45′ ጫላ ድሪባ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

90′ ሙሀጅር መኪ ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

82′ ሙሃጅር ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ኳስ ኃይሌ እሸቱ ቢንሸራተትም ሊያገኘው አልቻለም፡፡ ግብ ሊሆን የሚችል መልካም አጋጣሚ ነበር፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አአ ከተማ
82′ ከነአን ማርክነህ ወጥቶ አማረ በቀለ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወልድያ
80′ ምንያህል ይመር ወጥቶ ሙሉጌታ ረጋሳ ገብቷል፡፡

75′ አአ ጫና ፈጥሮ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ ተደጋጋሚ የማዕዘን እና ቅጣት ምቶች በማግኘት ላይም ይገኛሉ፡፡

71′ ኃይሌ እሸቱ ከርቀት የተሻገረለትን ኳስ በደረቱ አብርዶ በግሩም ሁኔታ አዙሮ የመታው ኳስ ለጥቂት በግቡ ቋሚ ወጥቷል፡፡ ግሩም ሙከራ!

የተጫዋች ለውጥ – አአ ከተማ
69′ ፍቃዱ አለሙ በጉዳት ወጥቶ እሱባለው ሙሉጌታ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወልድያ
60′ ያሬድ ሀሰን ወጥቶ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! አአ ከተማ
58′ ዳዊት ማሞ በግሩም አጨራረስ አዲስ አበባ ከተማን አቻ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል፡፡

53′ ፍቃዱ አለሙ የሞከረውን ኳስ ቤለሊንጌ በጥሩ ቅልጥፍና አውጥቶታል፡፡

ቢጫ ካርድ!
46′
ምንያህል ይመር የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀርያው አጋማሽ በወልድያ መሪነት ተጠናቋል፡

በርካታ የውልድያ ደጋፊዎች በቀኝ ከማን አንሼ ተሰባስበው ክባቸውን እየያበረታቱ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!! ወልድያ
45′ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ ደረጄ ሲመልሰው ጫላ ድሪባ አግኝቶት በቀጥታ በመምታት ወልድያን መሪ አድርጓል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

ቢጫ ካርድ!
38′
ዳዊት ማሞ በምንያህል ይመር ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

35′ ታዬ የመታውን ኳስ አለማየሁ ሙለታ በእጁ ነክቷል በሚል የፍፁም ቅጣት ምት ቢጠይቁም ዳኛው የማዕዘን ምት ለወልድያ ሰጥተዋል፡፡


34′
ጨዋታው በቀዝቃዛ እንቅስቃሴው ቀጥሏል፡፡

25′ ቤሊንጌ የህክምና እርዳታ አግኝቶ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡

22′ ኤሚክሪል ቤሊንጌ የማዕዘን ምት ላይ በተፈጠረ ግጭት ተጎድቶ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል፡፡

18′ ጨዋታው በወልድያ የሜዳ ክፍል ላይ እየተደረገ ይገኛል፡፡

11′ ሙሃጅር መኪ የመታው ኳስ ለጥቂት በግቡ አናት ወጥቷል፡፡

10′ የዛሬው የአየር ሁኔታ ደመናማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለእንቅስቃሴ አመቺ ቢመስልም እስካሁን የሁለቱም እንቅስቃሴ ዝግ ያለ ነው፡፡

3′ አንዱአለም ነጉሴ ከሳጥን ውጪ የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በአአ ከተማው ፍቃዱ አለሙ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ለሚያጡ ሰዎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አሰላለፍ

98 ደረጄ አለሙ

81 አለማየሁ ሙለታ – 6 ጊት ጋትኮች 20 ሰይፈ መገርሳ – 2 እንየው ካሳሁን

80 ከነአን ማርክነህ 13 ዘሪሁን ብርሃኑ – 30 ሙሃጅር መኪ – 40 ዳዊት ማሞ

24 ፍቃዱ አለሙ 8 ኃይሌ እሸቱ


ተጠባባቂዎች

1 ተክለማርያም ሻንቆ
70 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ
77 አማረ በቀለ
83 ጸጋ አለማየሁ
60 እሱባለው ሙሉጌታ
80 አዳነ በላይነህ
7 ምንያምር ጴጥሮስ


የወልድያ አሰላለፍ

16 ኤሚክሪል ቢሌንጌ

3 ቢኒያም ዳርሰማ — 14 ያሬድ ዘውድነህ — 25 አዳሙ መሀመድ — 6 ዮሐንስ ኃይሉ

5 ያሬድ ሀሰን – 21 ሀብታሙ ሸዋለም – 28 ታዬ አስማረ – 8 ምንያህል ይመር

15 ጫላ ድሪባ – 2 አንዱአለም ንጉሴ


ተጠባባቂዎች

64 ዳዊት አሰፋ
4 ሙሉነህ ጌታሁን
10 ሙሉጌታ ረጋሳ
19 አለማየው ግርማ
20 ነጋ በላይ
23 ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ
11 በድሩ ኑርሁሴን

09:40 ሁለቱም ቡድኖች ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡


ዳኞች
ፌዴራል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ሲመራ ወንድማገኝ ሙሴ እና ማዕረግ ወንድሜነህ የአሸብር ረደቶች ናቸው፡፡ ሚካኤል አርአያ 4ኛ ዳኛ ሆኖ ይመራል፡፡


ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

አዲስ አበባ ከተማ | አሸነፈ | ተሸነፈ | አቻ

ወልድያ | አሸነፈ | አሸነፈ | አቻ


ግንኙነት
ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡


ደረጃ
ወልድያ 18 ነጥቦችን በመሰብሰብ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ አዲስ አበባ ከተማ በ9 ነጥቦች የሊጉ ግርጌ ላይ ይገኛል፡፡


ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን!

በ15ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ከተማ ከ ወልድያ የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ገፅ ላይ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!


Leave a Reply