ኬንያ 2018፡ የቻን ማጣሪያ ድልድል…

ኬንያ በ2018 ለምታስተናግደው የቶታል የአፍሪካ ሃገራት ዋንጫ (ቻን) ለማለፍ የሚደረጉት የማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል በጋቦን ርዕሰ መዲና ካፍ ዓርብ ምሽት ይፋ አድርጓል፡፡ 48 ሃገራት በማጣሪያ እንደሚሳተፉ ካፍ  ሲገልፅ በስድስት ዞኖች ተከፍለው ሃገራት የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በሃገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ በሚሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫው ለአምስተኛ ግዜ የሚሰናዳ ነው፡፡ በሰሜን ዞን ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነችው ቱኒዚያ በማጣሪያው ታትካተት ቀርታለች፡፡ በውድድሩ ታሳትፋ የማታውቀው ግብፅ በማጣሪያው የምትሳተፍ ይሆኗል፡፡ የቻን 2014 አሸናፊዋ ሊቢያ ዳግም ወደ ቻን ዋንጫው ለመመለስ አልጄሪያን መርታት ይጠበቅባታል፡፡ የምዕራብ አፍሪካ ዞን በሁለት ምድቦች ተከፍሏል፡፡ የቻን 2016 የፍፃሜ ተፋላሚዋ ማሊ በምድብ አንድ ስትካተት ጠንካራዎቹ ኮትዲቯር፣ ጋና እና ናይጄሪያ በምድብ ሁለት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በማዕከላዊ ዞን የሁለት ግዜ የቻን አሸናፊዋ ዲ.ሪ. ኮንጎ እና ካሜሮን ይገኛሉ፡፡ ዲ.ሪ. ኮንጎ ጎረቤቷን ኮንጎ ሪፐብሊክን የምትገጥም ይሆናል፡፡ በደቡብ ዞን የኮሳፋ አበል ሃገራት በማጣሪያው የሚሳተፉ ይሆናል፡፡ በምስራቅ እና መካከለኛው ከአዘጋጇ ኬንያ ጋር አብሮ የሚሳተፍ ሁለት ሃገራት ይኖራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ጅቡቲን በመግጠም የማጣሪያ ጨዋታዋን ትጀምራለች፡፡ በቻን 2014 እና 2016 ምስራቅ አፍሪካን የወከሉት ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

በቅድም ማጣሪያ ዙር እንዲጫወቱ የተካተቱት ቶጎ፣ ቤኒን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ሞሪሺየስ እና ሲሸልስ ናቸው፡፡ የምስራቅ እና መካከለኛው ዞን እንዲሁም የደቡብ ዞን የቅድመ ማጣሪያ ዙር ጨዋታዎች በሚያዚያ ወር ሲደረጉ የምራብ ዞን ምድብ ሁለት በቶጎ እና ቤኒን መካከል የሚደረገው ጨዋታ በሐምሌ ወር ይደረጋል፡፡ የሰሜን ዞን ጨዋታዎች በነሃሴ ወር፣ የምዕራብ ዞን ሁለቱም ምድቦች በሐምሌ እና ነሃሴ ወር፣ ማዕከላዊ ዞን በነሃሴ ወር፣ የምስራቅ እና መካከለኛው በሐምሌ ወር እንዲሁም የደቡብ ዞን ሐምሌ ወር የማጣሪያ ጨዋታዎቹ የሚጀምሩ ይሆናል፡፡ አዘጋጇን ኬንያን ጨምሮ 16 ሃገራት በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

 

የማጣሪያ ግጥሚያዎች ሙሉ ድልድል

የሰሜን ዞን

ግብፅ ከ ሞሮኮ

አልጄሪያ ከ ሊቢያ

 

የምዕራብ ዞን ምድብ 1

ሴራሊዮን ከ ሴኔጋል

ጊኒ ቢሳው ከ ጊኒ

ላይቤሪያ ከ ሞሪታንያ

ጋምቢያ ከ ማሊ

 

ምዕራብ ዞን ምድብ 2

የቶጎ እና ቤኒን አሸናፊ ከ ናይጄሪያ

ኒጀር ከ ኮትዲቯር

ቡርኪናፋሶ ከ ጋና

 

ማዕከላዊ ዞን

ኤኳቶሪያል ጊኒ ከ ጋቦን

ኮንጎ ሪፐብሊክ ከ ዲ.ሪ. ኮንጎ

ሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ከ ካሜሮን

 

ምስራቅ እና መካከለኛው ዞን

የሶማልያ እና ደቡብ ሱዳን አሸናፊ ከ ዩጋንዳ

ታንዛኒያ ከ ሩዋንዳ

ጅቡቲ ከ ኢትዮጵያ

ብሩንዲ ከ ሱዳን

 

ደቡብ ዞን

የማዳጋስካር እና ማላዊ አሸናፊ ከ ሞዛምቢክ

የሞሪሺየስ እና ሲሸልስ አሸናፊ ከ አንጎላ

ኮሞሮስ ከ ሌሶቶ

ናሚቢያ ከ ዚምባቡዌ

ቦትስዋና ከ ደቡብ አፍሪካ

ስዋዚላንድ ከ ዛምቢያ

Leave a Reply