በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ለብቻው መሪ መሆን ያስቻለውን ነጥብ ሲያገኝ ሲዳማ ቡና ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

አዲስ አበባ ላይ በ10፡00 የተገናኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ንግድ ባንክ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ንግድ ባንክ በናይጄርያዊው አጥቂ ፊሊፕ ዳውዚ የ2ኛ ደቂቃ ግብ መሪ መሆን ሲችሉ ምንተስኖት አዳነ በ58ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ፈረሰኞቹ ነጥብ ተጋርተው እንዲወጡ አድርጋለች፡፡

የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ39 ነጥብ ከሲዳማ ቡና በ1 ነጥብ ከፍ ብሎ ሊጉን ሲመራ ንግድ ባንክ በ33 ነጥብ 3ኛ ደረጃውን እንደያዘ ነው፡፡

ወልድያ ላይ ወልድያ ወላይታ ድቻን አስተናግዶ 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ላለመውረድ የሚያደርገውን ትግል ነፍዝ ዘርቷል፡፡ የወልድያን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ፍፁም ደስይበለው ነው፡፡

ባህርዳር ስታድየም ላይ ኤሌክትሪክን ያስተናገደው ዳሽን ቢራ በኤዶም ሆሶሮቪ እና የተሸ ግዛው ግቦች 2-1 አሸንፏል፡፡

አዳማ ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው አዳማ ከነማ 3-1 በማሸነፍ ዘንድሮ በሜዳው ያለመሸነፍ ሪኮርዱን ሲያስጠብቅ አርባምንጭ ከነማ ሙገር ሲሚንቶን 1-0 ሀዋሳ ላይ ደግሞ ሀዋሳ ከነማ መከላከያን 2-1 አሸንፈዋል፡፡

ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ39 ነጥቦች ሲመራ ሲዳማ ቡና በ38 ፣ ንግድ ባንክ በ33 ነጥቦች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡ የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የንግድ ባንኩ ፊሊፕ ዳውዚ በ14 ይመራል፡፡ ቢንያም በ13 ፣ ሳሚ ሳኑሚ በ12 ፣ ኤሪክ ሙራንዳ በ10 ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

ያጋሩ