-በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ዛሬ ኢትዮጵያ ቡና ደደቢትን 4-1 አሸንፏል፡፡ ደደቢት በዳዊት ፍቃዱ የ9ኛ ደቂቃ ግብ መምራት ቢችልም ኢትዮጵያ ቡናዎች ቢንያም አሰፋ በ25ኛው ፣ ኤፍሬም አሻሞ በ41ኛው ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ በ50 እና 91ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች 4-1 አሸንፈዋል፡፡
ድሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 31 በማድረስ 2ኛ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊሰ ያለውን ርቀት አጥብቧል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ 15ኛ ሳምንት ከሀሙስ አስከ እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡
-የብሄራዊ ቡድናችን ኮከብ ሳላዲን ሰኢድ ወደ ግብፁ ታላቅ ክለብ አል-አህሊ የሚያደርገው ጉዞ እርግጥ እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡ አህሊ ኢንፎ በትዊተር ገፁ እንዳስነበበው የዋዲ ዴግላው አጥቂ ወደ አህሊ ጉዞ ከጫፍ ደርሷል፡፡
{jcomments on}