ባህር ዳር ከተማ አማካይ አስፈረመ

የጣና ሞገዶቹ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በአንድ ዓመት ውል አስፈርመዋል።

በአዲሱ አሰልጣኛቸው አብርሃም መብራቱ እየተመሩ የቅድመ ውድደር ዝጅታቸውን በመከወን በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ባለ ልምዱ አማካይ ሃይማኖት ወርቁን ማስፈረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የቀድሞው የጅማ አባ ጅፋር፥ ሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ አማካይ ወልዋሎን ቢቀላቀልም በአካባቢው በተፈጠረው ችግር ያለፈውን የውድድር ዓመት ሳይጫወት ቆይቷል። ኃይማኖት ከቀድሞ ክለቡ ባህር ዳር ጋር ልምምድ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ ዕለት ለትውልድ ከተማው ክለብ የአንድ ዓመት ውል ፈርሟል።

ያጋሩ

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.