ሀድያ ሆሳዕና ቶጓዊውን ግብ ጠባቂ የግሉ አድርጓል

በኢትዮጵያ ረዘም ያለ ቆይታን ያደረገው ቶጓዊው ግብ ጠባቂ በይፋ ለሀድያ ሆሳዕና ፈረመ፡፡

በዝውውር ገበያው በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው እና የ15ን ተጫዋቾች ጉዳይ በዛሬው ዕለት የፈታው ሀድያ ሆሳዕና በዝውውር መዝጊያው ምሽት ቶጓዊውን ግብ ጠባቂ ሱሆሆ ሜንሳን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡

ከአምስት አመት በፊት የጋቦኑ ሲ ኤፍ ሞናናን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ሀዋሳ ከተማን በመቀላቀል በክለቡ የተሳኩ ዓመታትን ያሳለፈው ሜንሳህ በ2011 የውድድር ዘመን ወደ ወልቂጤ ከተማ አምርቶ ቆይታን ካደረገ በኋላ በድጋሚ ወደ ሀዋሳ ተመልሶ እስከ ተጠናቀቀው ዓመት ድረስ የተጫወተ ሲሆን በዛሬው ዕለት አመሻሽ በሀዋሳ ከተማ ካሰለጠነው ሙሉጌታ ምህረት ጋር በድጋማ በሀድያ ሆሳዕና የተገናኘበትን ዝውውር ፈፅሟል፡፡

ያጋሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published.