​በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ አአ ከተማ አሸንፏል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛው ዙር ተጠናቆ ተስተካካይ ጨዋታዎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ 
በምድብ ለ 3ኛው ሳምንት ጨዋታ እንዲያደርጉ ፕሮግራም ወጥቶላቸው የነበረው ሲዳማ ቡና እና አአ ከተማ በዝግጅት ጊዜ እጥረት ምክንያት ተራዝሞ የነበረ ሲሆን ትላንት ይርጋለም ላይ ባደረጉት ጨዋታ እንግዳው አዲሱ  አበባ ከተማ 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በክረምቱ ሲዳማ ቡናን ለቃ አአ ከተማን የተቀላቀለችው ተራማጅ ተስፋዬ በቀድሞ ክለቧ ላይ ስታስቆጥር አስናቀች ቲቤሶ ሌላኛውን ጎል አስቆጥራለች፡፡ 

ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተማ ደረጃውን ወደ 4ኛ ሲያሻሽል ሲዳማ ቡና ባለበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 1ኛው ዙር ጨዋታዎች ሙሉ ለሙሉ የሚጠናቀቁት ቅዳሜ የካቲት 4 ቀን 2009 በሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ መካከል በሚደረገው የ1ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ይሆናል፡፡

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዙር ግምገማ ሀሙስ የካቲት 2 በአዳማ የሚካሄድ ሲሆን የምድብ ሀ 2ኛው ዙር ውድድር የካቲት 6 ፤ የምድብ ለ ደግሞ የካቲት 11 እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያወጣው መርሃ ግብር ያሳያል፡፡

1 Comment

  1. ከፕሪምየር ሊግ ዉጪ ያሉ ዉጠቶችን እንደት ማግኘት ይቻላል?

Leave a Reply