ቻምፒየንስ ሊግ | ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ወደ ሲሸልስ የሚጓዙ 18 ተጫዋቾች ታውቀዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ የፊታችን ቅዳሜ ፕራስሊን ላይ ከኮት ዲኦር ጋር ላለበት የቶታል 2017 ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ 18 ተጫዋቾችን ለይቷል፡፡

ሐሙስ ወደ ሲሸልስ በሚያቀናው የ18 ተጫዋቾች ውስጥ መካተት ከቻሉት ተጫዋቾች መካከል አዲስ ፈራሚዎቹ ፕሪንስ ሲቬርኒሆ ዋንጎ እና ብሩኖ ኮኔ ይገኙበታል፡፡ ቡርኪናፋሶዋዊ ፕሪንስ በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ፈረሰኞቹን ቢቀላቀልም ቋሚ ውል ሳያፈርም ቀርቷል፡፡ ኮትዲቯራዊው አጥቂ ኮኔ ከሳምንታት በፊት ዝውውሩ የተጠናቀቀ በመሆኑ በቻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ መሰለፍ ይችላል፡፡

በግብ ጠባቂነት ዩጋንዳዊው ሮበርት ኦዶንካራ እና ሮበርት ባልነበረበት ጨዋታዎች ክለቡ በሚገባ ያገለገለው ፍሬው ጌትነት በስብስቡ ውስጥ ተካቷል፡፡ ምንያህል ተሾመ፣ ያስር ሙገርዋ እና ፍሬዘር ካሳ ደግሞ ከስብስቡ የተዘለሉ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡ ምንያህል በጉዳት ምክንያት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ሳይችል መቅረቱ ይታወሳል፡፡

ሙሉ ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች

ፍሬው ጌትነት፣ ሮበርት ኦዶንካራ

ተከላካዮች

ደጉ ደበበ፣ ሳላዲን ባርጌቾ፣ አስቻለው ታመነ፣ አበባው ቡታቆ፣ መሃሪ መና፣ አንዳርጋቸው ይላቅ

አማካዮች

ናትናኤል ዘለቀ፣ ምንትስኖት አዳነ፣ አብዱልከሪም ኒኪማ፣ በሃያሉ አሰፋ፣ ፕሪንስ ሲቬርኒሆ ዋንጎ፣ ተስፋዬ አለባቸው

አጥቂዎች

አዳነ ግርማ፣ ሳላዲን ሰዒድ፣ አቡበከር ሳኒ፣ ብሩኖ ኮኔ

1 Comment

Leave a Reply