ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

​​​ FT ኢት. ንግድ ባንክ  0 2 ሀዋሳ ከተማ

           68′ ቢኒያም ሲራጅ (OG), 80′ ጃኮ አራፋት  


ሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ዙር መጨረሻ ጨዋታውን ድል በማድረግ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ውጤት አስመዝግቧል !

 90+1 የተጨዋች ለውጥ ሀዋሳ ከተማ

ጃኮ አራፋት ሲወጣ ወንደሰን ማዕረግ ገብቷል 

90 ‘ ጭማሪ ደቂቃ 3 !

88′ ጨዋታው ፍጥነት የታከለበት የማጥቃት ምልልስ በሁለቱም ቡድኖች በኩል እየታየበት ይገኛል ።

 86′ ፒተር በመልሶ ማጥቃት በቀኝ በኩል ይዞ የገባውን ኳስ አክርሮ ቢሞክርም ኳስ ወደ ላይ ተነስታለች ።

83′ ዳንኤል ደርቤ ከፍሬው ሰለሞን የተቀበለውን ኳስ ከቀኝ መስመር በቅርበት ሞክሮ ሙሴ ለጥቂት አድኖበታል ።

81′ የተጨዋች ለውጥ ሀዋሳ ከተማ

ዮሀንስ ሴጌቦ ገብቶ ታፈሰ ሰለሞን ወጥቷል

80 ‘ ጎል ሀዋሳ ከተማ ጃኮ አራፋት !

በታፈሰ ሰለሞን ከቀኝ መስመር የተነሳችውን ኳስ ጃኮ ከተከላካዮች ጀርባ በመነሳት ጎል አድርጓታል 

78′ ደስታ ዮሀንስ ከግራ መስመር ለጎሉ እጅግ ቅርብ ለነበረው ዮናታን ከበደ ያለቀ ኳስ አቀብሎት ዮናታን ሳይጠቀምበት ሲቀር ጋዲሳ ደርሶ በቀጥታ ሲሞክር ወደላይ ተነሳበት 

77′ የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 

ኤፍሬም ካሳ በጌቱ ረፌራ ተተክቷል ።

74′ ጃኮ አራፋት ከሳጥን ውጪ አክርሮ ሲሞክር አንትንህ ገ/ክርስቶስ ተደርቦ አውጥቶበታል ።

68′ ጎል ሀዋሳ ከተማ! ቢኒያም ሲራጅ በራሱ ግብ ላይ

ታፈሰ ሰለሞን ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ቢንያም ሲራጅ  ለማዳን ሲሞክር በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል !

67′ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን ከተጠባባቂ ወንበር ላይ ያልተገባ ባህሪ በማሳየት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

64′ ሳሙኤል ዮሀንስ ከመሀል ሜዳ ያሻገረው ኳስ ተጠቅሞ ዮናስ ገረመው ለብቻው ወደ ሀዋሳ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ቢገባም ሜንሳ ሶሆም ቀድሞ አድኖበታል ።

60′ የተጨዋች ለውጥ ሀዋሳ ከተማ

ዮናታን ከበደ በሔኖክ ደሌቦ ተቀይሮ ወደሜዳ ገብቷል 

56′ ንግድ ባንኮች በቀኝ መስመር በቢንያም በላይ አማካይነት ወደ ሀዋሳዎች ሳጥን ለመግባት ያደረጉት ሙከራ በሜንሳ ሳሆሆ ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል ።

54′ መላኩ ወልዴ መሀል ሜዳ ላይ በሳሙኤል ዮሀንስ ላይ በፈፀመው ጥፋት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

53′ ፒተር ንዋድኬ ከግራ መስመር የተሻማውን ኳስ በግንባሩ ሞክሮ በጎን ወደውጪ ወጥቶበታል ።

50′ ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ሀዋሳዎች በተሻለ ወደተጋጣሚያቸው የግብ ክልል ለመቅረብ እየሞከሩ ነው ።

47′ ጃኮ አራፋት ከሀዋሳዎች ሳጥን ግማሽ ጨረቃ ላይ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል ።

46′ ሁለተኛው የጨወታ አጋማሽ ተጀመረ !

የመጀመሪያው ግማሽ ተጠናቋል !

45′ ጭማሪ ደቂቃ 3 !

36′ በጨዋታው እስካሁን ምንም የተለየ ነገር እየታያ አይደለም ። የቡድንምቹ እንቅስቃሴ እንደተቀዛቀዘ ቀጥሏል ። 

30′ ንግድ ባንኮች በተሻለ በመስመሮች እና በቆሙ ኳሶች ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ነው ። ሀዋሳ ከተማዎች ኳስ መስርተው ሰብረው ለመግባት የሚያረጉት ጥረት ስኬታማ እየሆነላቸው አይደለም ።

26′ ፒተር ንዋድኬ ከቢኒያም በላይ የተቀበለውን ኳስ ወደ ሳጥን ይዞ ገብቶ በግራ እግሩ ቢሞክርም  ኳሷ ለጥቂት ወደውጪ ወጥታለች ።

25′ የተጨዋች ቅያሪ ንግድ ባንክ 

ሳሙኤል ዮሀንስ ጉዳት ያጋጠመውን ፍቅረየሱስን ቀይሮ ገብቷል ።

23′ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን ተጎድቶ ወጥቷል ። የተጨዋች ቅያሪ እስኪደረግ ንግድ ባንኮች በጎዶሎ ሰው እየተጫወቱ ነው ።

20′ እስካሁን ባለው የጨዋታ ሂደት ሁለቱ ቡድኖች ተመጣጣኝ የመሀል ሜዳ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ። ነገር ግን በጣም ለጎል የቀረቡ ሙከራዎች እየታዩ አይደለም ።

13′ ፍሬው ሰለሞን ከንግድ ባንኮች ሳጥን ጠርዝ ላይ የሞከረውን ኳስ ሙሴ በቀላሉ ይዞታል ።

10′ ጨዋታውን ጥቂት ተመልካችምች ብቻ በስታድየም ተገኝተው እየተከታተሉት ይገኛሉ። አብዛኛው እንቅስቃሴ መሀል ሜዳ ላይየተወሰነ ሆኗል። 

7′ ቢኒያም በላይ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ፍቅረየሱስ በግንባሩ ሞክሮ ወደላይ ወጥቶበታል ።

2′ ዳንኤል ደርቤ በግምት ከ 30 ሜትር የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል ።

1′ ጨዋታው ተጀምሯል ።

 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ 

29 ሙሴ ገ/ ኪዳን

7 ኣንኤል አድሀኖም – 12 አቤል አበበ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 13 አንተነህ ገብረክርስቶስ

4 ጂብሪል አህመድ 

2 ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን – 21 ዮናስ ገራመው – 8 ኤፍሬም ካሳ –  80 ቢንያም በላይ

 11 ፒተር ንዋድኬ 

ተጠባባቂዎች

33 ፋሪስ አለዊ

17 ሳሙኤል ዮሀንስ

26 ጌቱ ረፌራ

19 ፍቃዱ ደነቀ

44 አዲሱ ሰይፉ

6 አምሀ በለጠ

5 ቶክ ጀምስ

የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ 

1 ሶሆሆ ሜንሳህ

7 ዳንኤል ደርቤ – 13 መሳይ ጳውሎስ – 22 መላኩ ወልዴ – 12 ደስታ ዮሀንስ

5 ታፈሰ ሰለሞን – 24 ኃይማኖት ወርቁ – 25 ሔኖክ ድልቤ

10 ፍሬው ሰለሞን – 15 ጃኮ አራፋት – 11 ጋዲሳ መብራቴ

ተጠባባቂዎች

30 አላዛር መርኔ

4 አስጨናቂ ሉቃስ

26 ወንደሰን ማዕረግ

19 ዮሀንስ ሌጌቦ

9 እስራኤል እሸቱ

16 ዮናታን ከበደ

27 ፍርድአወቅ ሲሳይ

በመቀጠል የቡድኖቹን አሰላለፍ እናቀርባለን

11: 20 ተጨዋቾቹ ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል

11፡ 10 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች እያሟሟቁ ይገኛሉ ።


ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

ኢት. ንግድ ባንክ | አቻ | ተሸነፈ | ተሸነፈ

ሀዋሳ ከተማ  አቻ | አሸነፈ | ተሸነፈ | 


ደረጃ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ13 ነጥቦች 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ሀዋሳ ከተማ ደግሞ በ11 ነጥቦች 15 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡


ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን!

በ2ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ገፅ ላይ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

1 Comment

Leave a Reply