ፌዴሬሽኑ ግራ በተጋባ አካሄዱ ቀጥሏል

ማርያኖ ባሬቶ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በድጋሚ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶን አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል፡፡ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ መጥተው ድርድር ሲያደርጉ የቆዩት ጎራን ስቲቫኖቪች ከስምምነት ሊደርሱ ባለመቻላቸው ከ15 ቀን በፊት የገፋቸው አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶን ለመቅጠር ከውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡

በፌዴሬሽኑ ላይ እርግጠኛ መሆን አስቸጋሪ ቢሆንም ፖርቱጋላዊው አወዛጋቢ አሰልጣኝ በቀጣዮቹ ቀናት አዲስ አበባ በመምጣት ቀሪዎቹን ድርድር አካሂደው ከስምምነት ላይ ከደረሱ ቀጣዩ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ይሾማሉ፡፡

ፌዴሬሽኑ ለውሳኔ ያበቃው ማርያኖ ባሬቶ ጎራን ስቲቫኖቪች ከጠየቁት ደሞዝ በግማሽ ቀንሰው ወርሃዊ 15 ሺህ ዶላር ደሞዝ በማቅረባቸውና የአሰልጣኝ ቡድናቸውን በኢትዮፕያውያን ለማዋቀር በመስማማታቸው ነው ተብሏል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ