​የኢትዮጵያ ሴቶች ዋንጫ [ጥሎ ማለፍ] ድልድል ይፋ ሆኗል 

የኢትዮጵያ ሴቶች ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ውድድር የዕጣ ማውጣት ስነስርአት ሀሙስ በአዳማ ከተማ የባ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ 

በዘንድሮው ውድድር ላይ ሁሉም (20) የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች የሚካፈሉ ሲሆን በወጣው እጣ መሰረት 12 ቡድኖች በቀጥታ ወደ ሁለተኛው ዙር ሲያልፉ 8 ቡድኖች የመጀመርያው ዙር ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡

ማስታወሻ

የጥሎ ማለፉ የውድድር ፕሮግራሞች ቀን እና ሰአት ከሊጉ ጨዋታዎች ጋር የማይጣጣም ከሆነ ለውጥ ሊደረግበት እንደሚችል ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡
የውድድሩ ድልድል ይህንን ይመስላል፡-

1ኛ ዙር 

ሀሙስ የካቲት 16 ቀን 2009

09:00 ጥረት ከ አቃቂ ቃሊቲ (አአ ስታድየም)

11:30 አአ ከተማ ከ ደደቢት (አአ ስታድየም)

08:00 ኤሌክትሪክ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አበበ ቢቂላ)

10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ (አበበ ቢቂላ)

2ኛ ዙር 

የካቲት 17 ቀን 2009

09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢ.ወ.ስ. አካዳሚ (አአ ስታድየም)

11:30 ቦሌ ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ (አአ ስታድየም)

08:00 አዳማ ከተማ ከ ቅድስት ማርያም (አበበ ቢቂላ)

10:00 ልደታ ከ ጌዲኦ ዲላ (አበበ ቢቂላ)

የካቲት 21 ቀን 2009

09:00 የጥረት እና አቃቂ ቃሊቲ አሸናፊ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)

11:30 የአአ ከተማ እና ደደቢት አሸናፊ ከ ሲዳማ ቡና (አአ ስታድየም)

08:00 የኤሌክትሪክ እና ንግድ ባንክ አሸናፊ ከ አርባምንጭ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ አሸናፊ ከ ሀዋሳ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

ያጋሩ

Leave a Reply