የ2017 ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ ዛሬ ይጀመራል

​በቶታል ስፖንሰር አድራጊነት የሚካሄደው የ2017 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ዛሬ ካምፓላ እና በቻር ላይ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል፡፡ 

የዩጋንዳው ቻምፒዮን ኬሲሲኤ በሜዳው የአንጎላውን ፕሪሜሮ ደ አጎስቶን ሲያስተናግድ ለውድድሩ እንግዳ የሆነው የአልጄሪያው ጄኤስ ሳዎራ የናይጄሪያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊውን ኢንጉ ሬንጀርስን ይገጥማል፡፡ የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሜ ከሲሸልሱ ኮት ዲ ኦር ጋር በፕራስሊን ይጫወታል፡፡

የፊሊፕ ኦሞንዲ ስታዲየም ለጨዋታው ቡቁ ነው በመባሉ የኪሲሲኤን እና ፕሪሜሮ አጎስቶን ጨዋታ ያስተናግዳል፡፡ የስታዲም የተመልካች የመያዝ አቅም 10ሺ ቢሆንም 5600 ተምልካቾች ብቻ ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ይፈቀድሏቸዋል ብሏል የዩጋንዳው ክለብ፡፡ ሁለቱም ክለቦች በቻምፒየንስ ሊጉ በተለያዩ ግዜያት የተሳተፉ ቢሆንም በውጤት ደረጃ የአንጎላው ክለብ በ1997 ወደ ምድብ የገባበት የተሻለ ውጤቱ ነው፡፡ ኬሲሲኤ ወደ ምድብ አልፎ አያውቅም፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ለክሬንሶቹ ጥሩ ግልጋሎት የሰጠው የግራ መስመር ተመላላሹ ጆሴፍ ኦቻያ ወደ ቡድኑ መመለስ የማጥቃት ሽግግሩን ለካምፓላው ክለብ ምቹ ያደርግለታል፡፡

ኢንጊ ሬንጀርስ ወደ ሰሜን አፍሪካ አቅንቶ ጄኤስ ሳዎራን ይገጥማል፡፡ ኢንጉ በናይጄሪያ ፕሪምየር ሊግ መጥፎ አጀማመር አድርጓል፡፡ የናይጀየሪያ ሊግ አሸናፊ ካደረጋቸውን 6 ጨዋታዎች 6 ነጥቦችን ብቻ በማሳካት ወራጅ ቀጠናው ላይ ይገኛል፡፡ ተጋጣሚው ጄኤስ ሶዎራ በ2008 የተመሰረተ ሲሆን በተመሰረተ 9 ዓመታት ውስጥ በአልጄሪያ ሊግ አንድ ጥሩ ተፎካካሪ መሆን ችሏል፡፡ ያለፈውን የውድድር ዓመት በሁለተኝነት ያጠናቀቀው ክለቡ በቻምፒየንስ ሊግ ሲሳተፍ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ነው፡፡ በውድድሩ ልምድ ባይኖረውም በ2016 ሌላኛው የአልጄሪያ ክለብ የሆነው ኤምኦ ቤጃያ ለመጀመሪያ ግዜ በተሳተፈበት የአፍሪካ ክለቦች ውድድር ላይ በኮንፌድሬሽን ዋንጫ ለፍፃሜ መድረሱ ለሳዎራም እንደመነሻሻ ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡

ዓርብ የካቲት 3

16፡00 – ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ) ከ ሲዲ ፕሪሜሮ ደ አጉስቶ (አንጎላ) (ፍሊፕ ኦሞንዲ ስታዲየም)

19፡00 – ዩነስ ስፖርቲቭ ደ ላ ሳዎራ (አልጄሪያ) ከ ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) (ስታደ ኦገስት 20 1955)

Leave a Reply