​ባህርዳር ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ የሜዳቸውን ጨዋታዎች የሚያደርጉባቸው ሜዳዎች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች የሆኑት ባህርዳር ከተማ እና ወልቂጤ ከተማን 2 ተከታታይ ጨዋታዎች በሜዳቸው እንዳይጫወቱ እና ከሚገኙበት ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ በሚገኝ ሜዳ እንዲጫወቱ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

ሁለቱ ክለቦች በ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተና ሊግ ጨዋታቸውን በሜዳቸው የሚያደርጉ በመሆናቸው ቅጣቱ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በዚህም ባህርዳር ከተማ ከ አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ጎንደር ላይ በአፄ ፋሲለደስ ስታድየም እሁድ 09፡00 ይጫወታል፡፡ 

በምድብ ለ ወልቂጤ ከተማ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ሀዋሳ ላይ እሁድ በ8፡00 ይደረጋል፡፡ ወልቂጤ አዲስ አበባ ላይ ለመጫወት ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም የአበበ ቢቂላ ስታድየም ተደራራቢ ጨዋታዎች የሚያስተናግድ በመሆኑ ወደ ሀዋሳ ተዘዋውሯል፡፡

የከፍተኛ ሊጉ የዚህ ሳምንት ፕሮግራም ይህንን ይመስላል፡-

ምድብሀ

[table “183” not found /]

ምድብ ለ

[table “184” not found /]

Leave a Reply