አዳነ ግርማ እና አቡበከር ሳኒ ስለ ኮት ዲ ኦሩ ጨዋታ ይናገራሉ

ፕራስሊን ላይ ቅዳሜ የሲሸልስ ባርክሌ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ኮት ዲ ኦር ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናግዳል፡፡ የፈረሰኞቹ የፊት መስመር ተሰላፊዎች አቡበከር ሳኒ እና አዳነ ግርማ ስጨዋታው እና ተያያዥ ጉዳዮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

“ቦርዱም፣ እኛም ሆነ ደጋፊው ብዙ ርቀት መጓዝ ነው የምንፈልገው” አዳነ ግርማ

ስለዝግጅት

“ትልቅ ዝግጅት ነው ያደረግነው፡፡ በአጠቃላይ መስከረም ላይ ነው ጠንካራ ዝግጅት የምንጀምረው ቢሆንም ግን የቻምፒየንስ ሊጉ አቀራረብ  ስለተቀየረ  ትልቅ ዝግጅት ነው ያደረግነው፡፡ ለምን አቀራረቡ ለእኛ እንደሚመች ዓይነት ሆኖ ነው እኛ ከጠነከርን በመጀመሪያ ከሜዳችን ውጪ እንደመጫወታችን ይህ አጋጣሚ በጣም ትልቅ ነው፡፡ ከሜዳ ውጪ ጥሩ ውጤት ይዘን ከመጣን ሃገራችን ላይ ከደጋፊያችን ጋር ጥሩ ነገር እናመጣለን ብዬ ነው ማስበው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስን ብቻ አይደለም የምንወክለው ሃገርንም ነው የምንወክለው ከዚህ አንፃር ትልቅ ሃላፊነት አለብን ብዬ ነው ማስበው፡፡”

የቻምፒየንስ ሊግ ጉዞ

“ቦርዱም፣ እኛም ሆነ ደጋፊው ብዙ ርቀት መጓዝ ነው የምንፈልገው፡፡ በእኛ እግርኳስ በኢንተርናሽናል መድረክ ብዙ ርቀት መጓዝ አልተለመደም፡፡ እኛ ይህንን ነገርለማድረግ ሁላችንም ተነሳስተን ነው ያለነው፡፡ እኛም፣ ደጋፊውም እና ሃላፊዎቻችንም ተነሳስተው ነው ያሉት፡፡ የተለየ ዝግጅት ነው ያደረጉልን ከዚህ አንፃር የደጋፊውም ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ሁሌ የሃገር ውስጥ የሚባል ነገር አለ፡፡ ስለዚህ በዚህ ውድድርም አንድ የተለየ ነገር ለማድረግ ሁላችንም ተዘጋጅተናል፡፡”

ስለተጋጣሚ ቡድን

“ከሜዳ ውጪ የሚወራው ሌላ ነገር ነው፡፡ እኛን ሜዳ ውስጥ ያለው ነገር ነው የሚያሳስበን ለምን 90 ደቂቃው ነው የሚወስነው፡፡ የዕለቱ ሁኔታ ነው የሚወስነው ኳስ፡፡ የምትገምተው ነገር አይደልም፡፡ ስለዚህ ከተጋጣሚያችን ጋር ላለብን ጨዋታ ትልቅ ዝግጅት ነው ያደረግነው፡፡”

“በቻምፒየንስ ሊግ ጥሩ ነገር ለመስራት አስባለው” አቡበከር ሳኒ

ስለጨዋታው

“ያው ሁልጊዜ እንደምንዘጋጀው ነው የተዘጋጀነው፡፡ ሃገር ውስጥ እንደምንዘጋጀው ነው ለዚህም ትኩርት የምንሰጠው፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ጥሩ እድል አለ ብለን ነው የምናስበው፡፡ ለዚህም እንደቡድን ጠንክረን እየሰራን ነው፡፡ ያለንን ነገር አሳይተን ዘንድሮ ላይ ያለነበረንን ታሪክ ለመቀየር እና ጥሩ ነገር ለመስራት ነው እያሰብን ያለነው፡፡”

“ከአላህ ጋር በመሆን ጥሩ ነገር ለማሳየት እጥራለው፡፡ በቻምፒየንስ ሊግ ጥሩ ነገር ለመስራት አስባለው፡፡”

 

Leave a Reply