ፌዴሬሽኑ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ መርጧል መባሉን አስተባበለ

የኢትየጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአዳማ ከተማውን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ቢዘገብም ፌዴሬሽኑ እስካሁን የአሰልጣኝ ምርጫ አለማድረጉን ለሚድያ በላከው መግለጫ አስተባብሏል፡፡

” ለኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ለመቅጠር በወጣው ማስታወቂያ መሰረት በቴክኒክና ልማት ቋሚ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ ያልተሰጠበት እና ያልታየ መሆኑን እንገልጻለን፡፡” ሲል ፌዴሬሽኑ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

Leave a Reply