መከላከያ ከ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ | ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

 FT  መከላከያ 1-0ዮንግ ስፖርትስ አ.

41′ አዲሱ ተስፋዬ 
————————————————————

ተጠናቀቀ!!!!

ጨዋታው በመከላከያ 1 0 አሸናፊነት ተጠናቋል !

90′ ጭማሪ ደቂቃ 4 !

88′ ጨዋታው አሁንም የተቀዛቀዘ  ሙከራ አልባ እንቅስቃሴ እያስተናገደ ይገኛል ።

85′ የተጨዋች ቅያሪ መከላከያ 

ማራኪ ወርቁ ወጥቶ ታመስገን ገ/ፃዲቅ ገብቷል ።

80′ በመጀመሪያው አጋማሽ ከብዙ አማራጮች የግብ ዕድሎችን ሲፈጥሩ የነበሩት መከላከያዎች አሁን ላይ ከኋላ በረጅሙ ለአስጥቂዎች በሚላኩ ኳሶች ላይ ጥገኛ ሆነዋል ።

79′ የተጨዋች ቅያሪ መከላከያ 

በሀይሉ ግርማ በ ኦጉታ ኦዶክ ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል ።

78′ የተጨዋች ቅያሪ መከላከያ 

ቴውድሮስ ታፈሰ በሳሙኤል ሳሊሶ ተተክቷል ።

75′ ጨዋታው በገፋ ቁጥር መከላከያዎች ወደኋላ እያፈገፈጉ ይገኛሉ ። በዚህም ምክንያት ለተጋጣሚያቸው ሰፊ የመጫወቻ ሜዳ ሰጥተዋል ።

73′ የተጨዋች ቅያሪ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ

የመስመር አማካዩ እና የቡድኑ አንበል ንቶንብ ንጎም ሲወጣ ግሬስ ታማ ወደማዳ ገብቷል ።

69′ ዮንግ ስፖርቶች የሚሰነዝሩት ጥቃት በተደጋጋሚ ከጨዋታ ውጪ እየሆነ ይገኛል ። 

65′ መከላከያዎች በተደጋጋሚ የመልሶ ማጥቃት ዕድሎችን እያገኙ ቢሆንም ከኋላ የሚነሱት ኳሶች ያልተመጠኑ በመሆናቸው እየባከኑ ይገኛሉ ።

63‘ የተጨዋች ቅያሪ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ

የአጥቂ አማካዩ ንዶንጎ ጋሌባ ወጥቶ ሮናልድ ንጋሌ ገብቷል ።

61′ ቢጫ ካርድ !

ቴውድሮስ በቀለ በእንቅስቃሴ መሀል  በሰራው ጥፋት ኳስ ወደውጪ ስትወጣ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

60′ ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር ጨዋታው በመጠኑ የተቀዛቀዘ ይመስላል ። ዮንግ ስፖርቶች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስዱም መከላከያዎች በቀኝ መስመር ያደላ መልሶ ማጥቃት እያደረጉ ነው ።

59′ አዲሱ ወደሜዳ ተመልሷል በሀይሉ ግርማም ቀለል ያለ ጉዳት ገጥሞት ወጥቶ የነበረ ቢሆንም እሱም ወደ ሜዳ ተመልሷል ።

58′ የተጨዋች ቅያሪ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ

ጁል ዲቲች የመስመር አማካዩን ዲዮቤል ቤንዚን ተክቶ ወደሜዳ ገብቷል ።

55′ አዲሱ ተስፋዬ በደረሰበት ግጭት የህክምና እርዳታ ሊደረግለት ከሜዳ ወጥቷል ።

50′ ዮንግ ስፖርቶች ጫና ፈጥረው በመጫወት ላይ ይገኛሉ ። የጨዋታው እንቅስቃሴም ወደ መከላከያዎች ሜዳ አመዝኗል ። 

48′ መከላከያዎች አሁንም በሁለት አጋጣሚዎች ያገኟቸውን የማዕዘን ምቶች ለመጠቀም ያደረጉት ጥረት መላካም የሚባል ነበር ። ግብ ባያስቆጥሩም የተጋጣሚያቸውን ተጨዋቾች ጫና ውስጥ መክተት ችለው ነበር ።

46′ ሁለተኛው አጋማሽ በመከላከያዎች አማካይነት ተጀምሯል ።

የመጀመሪያው አጋማሽ በመከላከያ 1 – 0 መሪነት ተጠናቀቀ ።

45+1 ሲያ ሳንጉ ከግራ መስመር ያሻማውን የማዕዘን ምት የመሀል ተከላካዩ ኦሊቨር ቴቼንግ በግንባሩ ቢሞክርም ኳሷ በግቡ አግዳሚ ወጥታለች ።

45′ ጭማሪ ደቂቃ 2 

41 ‘ ጎል መከላከያ አዲሱ ተስፋዬ !!!!

ከቀኝ መስመር የተሻማውን የማዕዘን ምት የመሀል ተከላካዩ አዲሱ ተስፋዬ በግንባሩ በመግጨት የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል ።

39′ በግምት ከ 20 ሜትር ርቀት ላይ ሳሙኤል ሳሊሶ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል ።

38′ ንዶንጎ ጋሌባ ከፍፁም ቅጣት ምት ውጪ አክርሮ የሞከረው ኳስ በአቤል ማሞ ተይዞበታል ።

36′ የተሻ ግዛው በቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሳሙኤል ታዬ ከግቡ አፋፍ ላይ ቢሞክርም ግብ ጠባቂው ይዞበታል ። በጣም ለግብ የቀረበ አጋጣሚ ነበር ። ሳሙኤል ታዬ ኳሷን ባለመጠቀሙ ከፍተኛ ቁጭት ታይቶበታል ።

35′ የመሀል አማካዩ ሪቻርድ ኢቦንጉ ከሳጥን ውጪ በቀጥታ ይሞከራትን ኳስ አቤል በቀላሉ ይዞበታል ። 

30′ ቀኝ መስመር ላይ ሁለት የዮንግ ስፖርትስ ተጨዋቾች ተጋጭተው ወድቀው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ።

28′ በጨዋታው የሚደረጉ የግብ ሙከራዎች ቁጥር ቢቀንስም የጨዋታው ፍሰት ግን አሁንም ፈጠን እንዳለ ቀጥሏል። የካሜሮኑ ቡድንም እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ ማጥቃትን መሰረት ያደረገ አጨዋወት እየተገበረ ይገኛል ።

26 ‘ ቢጫ ካርድ !

የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኤሊቪስ ውም በሳሙኤል ሳሊሶ ላይ በሰራው ጥፋት የመጀመሪያውን ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

19′ የተሻ ግዛው በግራ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ወደ ውስጥ ለሳሙኤል ታዬ ሲልክለት ሳሙኤል ታዬ ለ ሳሙኤል ሳሊሶ በጥሩ ሁኔታ አመቻችቶለት ሳሙኤል ሳሊሶ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ አክርሮ ቢሞክርም ኳስ በግቡ አናት ወጥታለች ። የሚያስቆጭ አጋጣሚ !

15′ ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች በኩል ቶሎ ቶሎ ወደግብ ሚደረስበት እና ሙከራዎች ሚደረጉበት ሆኖ ቀጥሏል ። እስካሁን ባለው ሁኔታ ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተመለከትን ነው ።

14 ‘ የቀኝ መስመር አማካዩ ዲዮቤን ቤንዚ ከመዕዘን ምት የተሻገረለትን ኳስ በእግሩ ቢሞክርም ወደላይ ወጥቶበታል ።

13′ የቀን መስመር ተከላካዩ ሽመልስ ተገኝ ከርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አግዳሚ ወጥቷል ።

12′ የተሻ ግዛው  ሳሙኤል ሳሊሶ ከመሀል ሜዳ ያሻገረለትን ድንቅ ኳስ አገባው ተብሎ ቢጠበቅም ሙከራውን በግብ ጠባቂው ተይዞበታል ።

9′ የፊት አጥቂው ፌስተስ አሳንጎ ከተከላካዮች በረጅሙ የተላከለትን ኳስ ተጠቅሞ ከ አቤል ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝ ሙከራው ከኢላማ ውጪ ሆናበታለች ።

8′ ሚካኤል ​ደስታ ከሳሙኤል ታዬ ጋር ተቀባብሎ ከሳጥን ውስጥ የመታትንኳስ ግብ ጠባቂው ንቤሞ ሊዮፖልድ ይዞበታል ።

6′ ሳሙኤል ሳሊሶ ከረጅም ርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወጥቷል ።

5′ ዲዮቤን ቤንዚ በቀኝ መስመር ወደውስጥ መሬት ለመሬት ያሻገራትን ኳስ አደጋ ከመፍጠሯ በፊት አቤል ማሟ ይዟታል ።

2′ ማራኪ ወርቁ ከመሀል የተሻገረለትን ኳስ ይዞ ከተከላካዮች ጀርባ ቢገባም ሙከራ ከማድረጉ በፊት በግብ ጠብቂው ተቀድሟል ።

1’ ጨዋታው በእንግዳው ቡድን አማካይነት ጀምሯል ! መከላከያ ከቀኝ ወደግራ ዮንግ ስፖርትስ ከግራ ወደቀኝ ያጠቃሉ ።

09 ፡ 58 የክብር እንግዶች የቡድኖቹን ተጨዋቾችን እየተዋወቁ ይገኛሉ ።

የመከላከያ አሰላለፍ

1 አቤል ማሞ

2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 4 አወል አብደላህ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ 

19 ሳሙኤል ታዬ – 21 በሀይሉ ግርማ – 13 ሚካኤል ደስታ – 9 ሳሙኤል ሳሊሶ

7 ማራኪ ወርቁ – 10 የተሻ ግዛው

ተጠባባቂዎች

22 ይድነቃቸው ኪዳኔ

17 ምንተስኖት ከበደ

11 ካርሎስ ዳምጠው

15 ቴዎድሮስ ታፈሰ

26 አጉታ ኦዶክ

27 ተመስገን ገ/ፃዲቅ 

28 ሚሊዮን በየነ

የዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ አሰላለፍ

30 ምቤሙ ሊዮፖልድ

18 ሚካኤል ንዶንብ – 27 ኤልቪስ ውም – 6 ኦሊቨር ቴቼንግ – 22 ብሩኖ ዮዋን 

13 ሪቻርድ ኢቦንጉ – 8 ሲያ ሳንጉ

11 ዲዮቤን ቤንዚ – 7 ንዶንጎ ጋሌባ – 14 ንቶንብ ንጎም  

 10 ፌስተስ አሳንጎ

ተጠባባቂዎች 

16 ሄርማን ሀላ

15 ሮላንድ ንጋሌ

2 አሊም ዳዎዳ

3 ጁል ዲቲች 

17 ኢማኑኤል ቻይ

19 ያኒክ ዬንጋል 

25 ግሬስ ታሞ            

          

09 45 ተጨዋቾቹ ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል በመቀጠል የሁለቱን ቡድኖች አሰላለፍ ይዘን እንመለሳለን ።

09 ፡ 30 የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ሰነታቸውን እያሟሟቁ ይገኛሉ ።

ባለፉት አራት አመታት ውስጥ ሶስት ጊዜ በዚህ የሀጉሪቱ ውድድር ላይ መሳተፍ የቻለው መከላከያ ባለፉት ሁለት አመታት በ ኬንያው ኤ ኤፍ ሲ ሊኦፓርድስ 4 – 1  እንዲሁም በግብፁ ምስር አል ማቃሳ 6 – 1 በሆኑ አጠቃላይ ውጤቶች በመሸነፍ በመጀመሪያው ዙር ከውድድሩ መሰናበቱ ይታወሳል ። ክለቡ በአምናው የኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ለፍፃሜ በመድረሱም በዘንድሮው የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የመሳተፍ ዕድሉን አግኝቷል ።

የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን ክለብ የሆነው ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ 2004 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ላይም ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈው በ 2014 ዓ.ም ነበር። ክለቡ አምና በሀገሪቱ የሊግ ውድድር ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ዘንድሮም በሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።  ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ  የመጨረሻዎቹን ሶስት የሊግ ጨዋታዎቹን ማሸነፍ ችሏል ። 

ሠላም ውድ አንባቢዎቻችን !

ዛሬ 10 ሰዐት ላይ በሚጀምረው ጨዋታ የኢትዮጵያው መከላከያ ከካሜሮኑ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ ጋር የሚያደርገውን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ከአዲስ አበባ ስታድየም በመሆን ልናስነብባቸሁ ተዘጋጅተናል ። 

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !

Leave a Reply