ሀዋሳ ከተማ ምስጋናው ወልደዮሃንስን አስፈረመ

ሀዋሳ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የተለያየው ምስጋናው ወልደዮሃንስን ለ1 አመት ከ6 ወራት የሚቆይ ውል አስፈርሟል፡፡ በስምምነታቸው መሰረትም ምስጋናው በድሬዳዋ ይከፈለው የነበረውን ወርሃዊ ክፍያ በሀዋሳ ከተማም የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ፈጣኑ የመስመር አማካይ ምስጋናው ደቡብ ፖሊስን ለቆ ወደ ድሬዳዋ ከተማ በ2 አመተ ኮንትራት የተዛወረው በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ነበር፡፡ ሆኖም በድሬዳዋ ከተማ የተሰላፊነት እድል በማጣቱ ክለቡን እንደለቀቀ ታውቋል፡፡

Leave a Reply