በ15ኛው ሳምንት ዛሬ 2 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

15ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ተጀምሯል እስከ እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎችም ይቀጥላል፡፡

ትላንት በተደረገው ብቸኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መብራት ኃይል 1-1 ተለያይተዋል፡፡ መብራት ኃይሎች በ8ኛው ደቂቃ በበረከት ይስሃቅ ግብ 1-0 መምራት ቢችሉም በ66ኛው ደቂቃ ወሰኑ ማዜ በግሩም ሁኔታ ባስቆጠራት ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ደረጃቸውን ሳያሻሽሉ ባሉበት ለመርጋት ተገደዋል፡፡ በተለይም መብራት ኃይል ቢያሸንፍ ወገብ ላይ ከሚገኙ ክለቦች ጋር ያለውን ልዩነት ማጥበብ ይችል ነበር፡፡

ሊጉ ዛሬ አዲ አአባ ስታዲየም ላይ በሚደረጉ 2 ጨዋዎች ቀጥላል፡፡ በ9 ሰአት በ18 ነጥቦች 7ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው መከላከያ በ2 ነጥብ አንሶ የሚከተለው አርባምንጭ ከነማን ያስተናግዳል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመርያው ዙር ያለግብ አቻ የተለያዩ ሲሆን ሁለቱም ከውጤት ማጣት ቀውስ ለመውጣት ድሉን ይፈልጉታል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ሐረር ቢራን የሚያስተናግድበት ጨዋታ የመከላከያ እና አርባምንጭ ከነማ ፍልሚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ በአስተዳደራዊ ለውጥ ላይ የሚገኘው የምስራቁ ክለብ እና በዝውውር መስኮቱ ራሱን የጠገነው መድን በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ እንደመገኘታቸው ከወራጅ ቀጠና ለማምለጥ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ39 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ መድን በ8 ነጥብ የመ፣ጨረሻውን ደረጃ ይዟል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *