ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያን የሚገጥመውን ስብስቧን አሳውቃለች

በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያን የምትገጥመው ደቡብ አፍሪካ የ23 ተጫዋቾች ዝርዝሯን ይፋ አድርጋለች።

ምድቡን በአራት ነጥብ እየመራች የምትገኘው የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ቤልጅየማዊው ሆጎ ብሮስ ከቀናት በኃላ በደርሶ መልስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚኖራቸው ጨዋታዎች ስብስባቸውን ይፋ ሲያደርጉ ከዚምባቡዌ እና ጋና ጋር ለነበሯቸው ጨዋታዎች ከመረጧቸው ተጫዋቾች ጋር የሚመሳሰል ስብስብን ይፋ ሲያደርጉ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የግቡፁን ኃያል ክለብ አል አህሊን ክብረወሰን በሆነ ዋጋ የተቀላቀለውና እስካሁን ለክለቡ ይፋዊ ጨዋታዎችን ማድረግ ያልቻለው ፐርሲ ታኡን ግን ሳያካትቱ ቀርተዋል።

በስብስቡ ውስጥ ከተከላካዩ ለእስራኤሉ ሀፖኤል ቴልአቪቭ ከሚጫወተው ሲያንዳ ዡሉ ውጭ በውጭ ሀገር የሚጫወት ተጫዋች በስብስቡ ያልተካተቱ ሲሆን ወደ ደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሺፕ አዲስ ያደጉት ሴኩህኹኔ ዩናይትድ ሁለት ተጫዋቾች ማስመረጣቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብጠባቂዎች

ሮንዊን ዊልያምስ (ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ)
ቪሊ ሞትዋ (አማዙሉ)
ብሩር ቢቩማ (ካይዘር ቺፍስ)

ተከላካዮች

ሲድኒ ሞቤ (ሴኩህኹኔ ዩናይትድ)
ርሻኔ ዲ ሩይክ (ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)
ሲያንዳ ዡሉ (ሀፕዌል ቴላቪቭ)
ሞሳ ሌቡሳ (ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)
ናጃቡላ ንግኮጎቦ (ካይዘር ቺፍስ)
ሲፊሶ ሂላንቲ (ካይዘር ቺፍስ)
ቴሬንስ ማሼጎ (ኬፕ ታውን)

አማካዮች

ናጃቡሉ ብሉም (ካይዘር ቺፍስ)
ሞቶሆቢ ምቬላ (ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)
ቲቦሆ ሞኬና (ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ)
ዩሱፍ ማርት (ሴኩህኹኔ ዩናይትድ)
ኢታን ብሩክስ (ቲኤስ ጋላክሲ)
ታሀባኒ ዙክ (ጎልደን አሮውስ)
ጉድማን ሞስዬሌ (ኦርላንዶ ፓይሬትስ)

አጥቂዎች

ኤቪደንስ ማክጎፓ (ባሮካ)
ቪክቶር ሊቶሶዋሎ (ሮያል ኤኤም)
ታቢሶ ኩቱሜላ (ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)
ቦንጎኹሌ ሂሎንግዋኔ (ማርያዝበርግ)
ቪንሰንት ፑሌ (ኦርላንዶ ፓይሬትስ)
ሼጎፋትሶ ማባሳ (ኦርላንዶ ፓይሬትስ)