ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተክሉ ተስፋዬን አስፈረመ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ዳሽን ቢራ አጥቂ ተክሉ ተስፋዬን አስፈርሟል፡፡

ተክሉ በ2008 መጨረሻ ዳሽን ቢራን ከለቀቀ በኋላ አዲስ አበባ ከተማን ተቀላቅሎ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ቢያሳልፍም ሳይፈርም ቀርቶ ያለፉትን ወራት ጨዋታ ሳያደርግ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን ለኢትዮ ኤሌክትሪክ የአንድ አመት ውል ፈርሞ ቡድኑን ተቀላቅሏል፡፡

የታፈሰ ተስፋዬ ታናሽ ወንድም የሆነው ተክሉ በሚሌንየሙ መጀመርያ በኢትዮጵያ ቡና የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ዳሽን ቢራ ሌሎች የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው፡፡

ኤሌክትሪክ በሁለተኛው ዙር የአጥቂ መስመሩን ለማጠናከር እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ጋናዊ የአጥቂ መስመር ተጫዋች ለማስፈሰም በድርድር ላይ ይገኛል፡፡

ከኤሌክትሪክ ጋር በተያያዘ ዜና የውል ዘመኑ ተጠናቆ የነበረው ሴራሊዮናዊው ተከላካይ ሲሴይ ሀሰን ውሉን ለተጨማሪ ጊዜያት አድሷል፡፡ ኤሌክትሪክ ከጋናዊው ተከላካይ አብዱል ፋትዋ ሳይዱ ጋር እንደተስማማ ቢገለጽም በፌዴሬሽን ውል እንዳልፈረመ ታውቋል፡፡

 

Leave a Reply