4 የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ከጥሎ ማለፉ ራሳቸውን አገለሉ 

የኢትዮጵያ ጥሎማለፍ የ2009 የውድድር ዘመን ድልድል ማክሰኞ በሶዶ ከተማ መውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ 5 የከፍተኛ ሊግ እና 16 የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን ያካተተው ውድድር ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ የ1ኛ ዙር ጨዋታዎች እንዲጀመር ፕሮግራም ቢወጣም 4 የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በተለያዩ ምክንያቶች መወዳደር እንደማይችሉ በመግለጻቸው በአንደኛው ዙር የሚደረገው ጨዋታ አንድ ብቻ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ ፣ ፌዴራል ፖሊስ እና አራዳ ክፍለከተማ እንደማይሳተፉ ያሳወቁ ክለቦች ሲሆኑ ሽረ እንደዳስላሴ ብቻ በውድድሩ ላይ እንደሚሳተፍ ታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፋሲል ከተማ ፣ ወልድያ ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ጅማ አባ ቡና በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሽረ እንዳስላሴ ቅዳሜ 11:30 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም በሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚገባው ቡድን ይለያል፡፡

1ኛ ዙር

ቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2009

11:30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ሽረ እንዳስላሴ (አአ ስታድየም)

የ2ኛ ዙር ተጋጣሚዎች

(ቀን እና ሰአት ወደፊት ይገለጻል)

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ

መከላከያ ከ ሀዋሳ ከተማ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወልድያ

ፋሲል ከተማ ከ አዳማ ከተማ

ደደቢት ከ ጅማ አባ ቡና

አአ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከተማ

የሽረ እንዳስላሴ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሸናፊ ከ ኢትዮጵያ ቡና

Leave a Reply