ዳኛቸው በቀለ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቷል

ድሬዳዋ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አጥቂ ዳኛቸው በቀለን በውሰት ውል ማስፈረሙን አረጋግጧል፡፡ የቀድሞው የአዳማ ከተማ ተጫዋች እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ድረስ የድሬዳዋ ከተማን ማልያ ለብሶ የሚጫወት ይሆናል፡፡

ዳኛቸው በቀለ ለአዳማ ከተማ ከመፈረሙ በፊት በድሬዳዋ ከተማ የተጫወተ ሲሆን አምና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቢቀላቀልም የቋሚ ተሰላፊነት እድል ማግኘት አልቻለም ነበር፡፡

ዳኛቸው ለድሬዳዋ ከተማ በዝውውር መስኮቱ የፈረመ 4ኛው ተጫዋች ሆኗል፡፡ አማካዩ አድናን ቃሲም ፣ ጋናዊው ተከላካይ ኢማኑኤል ላሬያ እና ሌላው ጋናዊ አጥቂ ሀምዛ መሀመድ ለብርቱካናማዎቹ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

Leave a Reply