ኮንፌድሬሽን ዋንጫ፡ መከላከያ የመልስ ጨዋታውን ዱዋላ ላይ ያደርጋል

የኮንፌዴሬሽኑ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታዎች ትላንት መደረግ ሲጀምሩ የዲ.ሪ. ኮንጎው ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ በሜዳው የጋቦኑን አካንዳን በአጠቃላይ ውጤት 1-0 በመርታት ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡ ሬኔሳንስ ከሜዳው ውጪ ሊበርቪል ላይ ያለምንም ግብ አቻ መለያየቱን ተከትሎ በመልሱ ጨዋታ አሸንፎ ወደ አንደኛው ዙር እንደሚያልፍ ተጠብቆ ነበር፡፡

የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎቹ ዛሬ እና ነገ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡ የኢትዮጵያው መከላከያ ዛሬ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚን ከሜዳው ውጪ ዱዋላ ላይ ይገጥማል፡፡ መከላከያ አዲስ አበባ ላይ በአዲስ ተስፋዬ ግብ 1-0 የካሜሮን አቻውን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በመልሱ ጨዋታ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፈውን ውጤት ካገኘ በአንደኛው ዙር የቱኒዚያውን ሴፋክሲየንን ይገጥማል፡፡ ጦሩ ወደ ዱዋላ ዕረቡ እለት አምርቷል፡፡ ጨዋታውን በሚያደርግበት ስታደ ደ ላ ሪዩኒፊኬሽንም ደ ዱዋላም ላይ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የጋናው ቤቸም ዩናይትድ የአልጄሪያውን ኤምሲ አልጀርን አልጀርስ ላይ ይገጥማል፡፡ ቤቸም በሜዳው 2-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ የኬንያው ኡሊንዚ ስታርስ ከሜዳው ውጪ በሊቢያው አል ሂላል ቤንጋዚ የደረሰበትን ሽንፈት ለመቀልበስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡ የዩጋንዳው ቫይፐርስ ወደ ኮሞሮስ አቅንቶ ከቮልካን ክለብ ደ ሞሮኒን ጋር ይጫወታል፡፡ ሞሮኒ በመጀመሪያው ዙር ያለግብ አቻ በመለያየቱ በሜዳው ቫይፐርስን እንደሚያሸነፍ ተገምቷል፡፡ ሞኖሮቪያ ክለብ ቤርዌሪስ ጄኤስ ካቤሌን 3-0 በመርታቱ የመልሱ ጨዋታ ያቀለለለት ይመስላል፡፡

 

የቅድመ ማጣሪያ ዙር ጨዋታዎች

የአርብ ውጤት

ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 1-0 አካንዳ (ጋቦን) (1-0)

 

ቅዳሜ የካቲት 11 2009

15፡00 – ቮልካን ክለብ ደ ሞሮኒ (ኮሞሮስ) ከ ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) (0-0) (ስታደ ደ ሞሮኒ)

15፡00 – ሜሰጀር  ንጎዚ (ብሩንዲ) ከ ኬቪዚ (ዛንዚባር) (1-2) (ፕሪንስ ሉዊ ራዋጋሶሬ)

15፡00 – ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ) ከ አል ሂላል ቤንጋዚ (ሊቢያ) (ካሳራኒ ስታዲየም)

15፡00 – ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ) ከ ፓምፕልማውስስ (ሞሪሽየስ) (1-1) (ባአባብ ስታዲየም)

15፡30 – ካራ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) ከ መግረብ ደ ፌስ (ሞሮኮ) (0-3) (ስታደ አልፎንሶ ማሳባ ደባት)

15፡30 – ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን) ከ መከላከያ (ኢትዮጵያ) (0-1) (ስታደ ደ ላ ሪዩኒፊኬሽንም ደ ዱዋላም)

15፡30 – ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር) ከ ሳንአብል (ቡርኪናፋሶ) (0-0) (ስታደ ሮበርት ቻምፕሮ)

16፡00 – ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ) ከ ኦራፓ ዮናይትድ (ቦትስዋና) (1-0) (ሎባምባ ስታዲየም)

16፡30 – ኒያሪ ታሊ (ሴኔጋል) ከ አፔጄስ ደ ሞፎ (ካሜሮን) (0-1) (ስታደ ዴምባ ዲዮፕ)

16፡30 – ሴንት ሚሼል (ሲሸልስ) ከ አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን) (0-2) (ዩኒቲ ስታዲየም)

18፡00 – ዩኒዮ ዴስፖርቲቫ ዶ ሶንጎ (ሞዛምቢክ) ከ ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ) (0-1) (ስታዲዮ ናሲዮናል ዶ ዚምፔቶ)

20፡30 – ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) ከ ቤቸም ዩናይትድ (ጋና) (1-2) (ስታደ ጁላይ 5 1962)

 

እሁድ የካቲት 12 2009

15፡30 – ሬሲንግ ሚኮሚሴንግ (ኤኳቶሪያል ጊኒ) ከ ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) (0-2) (ስታዲዮ ናኮቶማ)

15፡30 – ራዮን ስፖርትስ (ሩዋንዳ) ከ አል ሳላም ዋኡ (ደቡብ ሰዱን) (4-0) (አማሆሮ ስታዲየም)

15፡30 – ሱፐርስፖርት ዮናይትድ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ኤልጌኮ ፕላስ (ማዳጋስካር) (0-0) (ሉካስ ማስተርፒስስ ሞርፒ ስታዲየም)

16፡00 – ዊኪ ቱሪስትስ (ናይጄሪያ) ከ አርኤስኤልኤኤፍ (ሴራሊዮን) (0-2) (ታፋዋ ባሌዋ ስታዲየም)

18፡00 – ዩኒየስ ስርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ) ከ ሞኖሮቪያ ክለብ ቤርዌሪስ (ላይቤሪያ) (0-3) (ስታደ ዱ ኖቬምበር 1)

19፡00 – አል መስሪ (ግብፅ) ከ ኢፊያኒ ኡባ (ናይጄሪያ) (0-1) (ኢስማኤሊያ ስተዲየም)

19፡00 – ኢትሃድ ደ ታንገር (ሞሮኮ) ከ ኤኤስ ዶነስ (ኒጀር) (2-1) (ግራንድ ስታደ ደ ታንግር)

Leave a Reply