የቻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ

የቶታል 2017 ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ዙር የመልስ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች በሚካሄዱ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ላይ ኮት ደኦርን ያስተናግዳል፡፡ ፕራስሊን ላይ በሳላዲን ሰዒድ ሁለት ግቦች ኮት ደኦርን የረቱት ፈረሰኞቹ የማሸነፍ ቅድመ ግምትን አግኝተዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ያልተጠበቁ ውጤቶችን ባስተናገደው ቻምፒየንስ ሊጉ ወደ አንደኛው ዙር ለማለፍ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይባቸው ጨዋታዎች ይኖራሉ፡፡ የዛምቢያው ዛናኮ በሜዳው ከሩዋንዳው ኤፒአር ጋር ያለግብ አቻ መለያየቱን ተከትሎ በመልሱ ጨዋታ ኪጋሊ ፈተና ይገጥመዋል፡፡ የዜስኮ ዩናይትድን የ2016 ውጤት ዛናኮ በአሁኑ ግዜ የመድገም አቅም ያለው አይመስልም፡፡ የሁለቱን አሸናፊ በመጀመሪያው ዙር የሚገጥመው የታንዛኒው ያንግ አፍሪካንስ እና የኮሞሮሱ ንጋያ ክለብ አሸናፊ ነው፡፡ ያንጋ በመጀመሪያው ጨዋታ ከሜዳው ውጪ 5-1 ማሸነፉ ተከትሎ የካሞሮሱ ክለብ የማለፍ ተስፋው የመነመነ ነው፡፡

ወደ ኤኳቶሪያል ጊኒ አቅንቶ ሶኒ ንጉማን በኬሌቺ ኦሶንዋ የመጨረሻ ደቂቃ ግብ 1-0 የረታው የሱዳኑ ኤል ሜሪክ አንድ እግሩን ወደ አንደኛው ዙር አስገብቷል፡፡ ሜሪክ ኦምዱሩማን ላይ ዳግም አሸንፎ ጨዋታውን እንደሚደመድም ይታሰባል፡፡ በቻምፒየንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ግዜ እየተሳተፈ የሚገኘው አልጄሪያው ጄኤስ ሳዎራ ከመጀመሪያ ዙር የመሰናበት እድሉ የሰፋ ነው፡፡ በሜዳው ከናይጄሪያው ኢንጉ ሬንጀርስ ጋር 1 አቻ መለያየቱ የመልሱን ጨዋታ ያከብድበታል፡፡

የዩጋንዳው ኬሲሲሰኤ ወደ አንጎላ አቅንቶ ፕሪሞሮ ደ አጉስቶን ይገጥማል፡፡ ኬሲሲኤ ካምፓላ ላይ በጠበበ ውጤት ማሸነፉ ለመልሱ ጨዋታ እንዳይቸግረው ተሰግቷል፡፡ የሪዮኒየን ደሴቱ ክለብ ሴንት ሉዊዘን ቤድቬስት ዊትስ ላይ ያልተጠበቀ የ2-1 አሸናፊ ነበር፡፡ ቤድቬስት ዊትስ ውጤቱን እንሚቀለብስ የሚነገር ቢሆንም ሴንት ሊዊዘን ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆን ተገምቷል፡፡ አምና የኬንያውን ሃያል ክለብ ከውድድር ያስወጣው የማዳጋስካሩ ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት ወደ ቦትስዋና አቅንቶ ታውንሺፕ ሮለርስን ይገጥማል፡፡ ሮለርስ ከሜዳው ውጪ አንድ ግብ ማስቆጠሩ በመልሱ ጨዋታ ተጠቃሚ ያደርገዋል፡፡ ኤኤስ ቪታ እና ፉስ ራባት ከሜዳቸው ውጪ ያስመሀዘቡት ውጤት በመልሱ ጨዋታ የማለፍ ቅድመ ግምትን እንዲያገኙ አድርጓቸዋል፡፡ ሊቢያ በፖለቲካ አለመረጋጋት ብትናጥም ክለቧ አል አሃሊ ትሪፖሊ ብዙዎችን ማስደመሙን ቀጥሏል፡፡ የሊቢያው መዲና ክለብ ታማሌ ላይ ዋ ኦል ስታርስን 3-1 በማሸነፉ ከወዲሁ ቱኒዚያ ላይ በሚካሄደው የመልስ ጨዋታ ለማለፍ የሰፋ እድል ይዟል፡፡

 

የቅድመ ማጣሪያ ዙር ጨዋታዎች

 

ቅዳሜ የካቲት 11

15፡30 – ኤፒአር ኤፍሲ (ሩዋንዳ) ከ ዛናኮ (ዛምቢያ) (0-0) (አማሆሮ ስታዲየም)

16፡00 – ኤኤስ ፋን (ኒጀር) ከ ኤኤስ ታንዳ (ኮትዲቯር) (0-3) (ስታደ ጄነራል ኤስኬ)

16፡00 – ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) ከ ንጋያ ክለብ (ኮሞሮስ) (5-1) (ዳሬሰላም ናሽናል ስታዲየም)

16፡00 – ታውንሺፕ ሮለርስ (ቦትስዋና) ከ ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት (ማዳጋስካር) (1-2) (ጋቦሮኒ ናሽናል ስታዲየም)

16፡30 – አትላባራ (ደቡብ ሱዳን) ከ ኮተን ስፖርት (ካሜሮን) (0-2)

18፡00 – ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ሴንት ሊዊዘን (ሪዩኒየን ደሴት) (1-2) (ሚልፓርክ ስታዲየም)

19፡30 – ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ) ከ ኤፍሲ ዮሃንሰን (ሴራሊዮን) (1-1) (ኮምፕሌክስ ስፖርቲፍ ሞላይ አል ሃሰን)

20፡00 – ኤል-ሜሪክ (ሱዳን) ከ ሶኒ ደ ኤላ ንጉማ (ኤኳቶሪያል ጊኒ) (1-0) (ኤል ሜሪክ ስታዲየም)

 

እሁድ የካቲት 12

14፡30 – አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ ዋ ኦል ስታርስ (ጋና) (3-1) (ስታደ ኦሎምፒክ ሜንዝ)

15፡00 – ቪታሎ (ብሩንዲ) ከ ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን) 0-2) (ፕሪንስ ሉዊ ራዋጋሶሬ)

15፡00 – ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ) ከ ሊኦሊ (ሌሶቶ) (0-0) (ናሽናል ስፖርትስ ስታዲየም)

15፡00 – ክለብ ፌሮቪአሪዮ ደ ቤራ (ሞዛምቢክ) ከ ዚማማቶ (ዛንዚባር) (1-2) (ቤራ ስታዲየም)

15፡15 – ኤኤስ ፖርት ሉዊ (ሞሪሽየስ) ከ ተስካር (ኬንያ) (1-1) (ኪዩርፓይፕ ስታዲየም)

15፡30 – ሰዌ ስፖርት (ኮትዲቯር) ከ ጋምቢያ ፖርትስ ኦቶሪቲ (0-1) (ስታደ ሮበርት ቻምፕሮ)

15፡30 – ዲያብልስ ኖይርስ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) ከ ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ (ቡርኪናፋሶ) (0-3) (ስታደ አልፎንሶ ማሳምባ ደባት)

15፡30 – ዩኤምኤስ ደ ሎም (ካሜሮን) ከ ኤሲ ሊዮፓርድስ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) (0-1) (ስታደ ደ ላ ሪዩኒፊኬሽን ደ ዱዋላ)

15፡30 – ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ሮያል ሊዮፓርድስ (ስዋዚላንድ) (1-0) (ኮምፕሌክስ ኦምኒስፖርትስ ስታደ ደ ማርትየርስ)

16፡00 – ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንርናሽናል (ናይጄሪያ) ከ ጄኤስ ሳዎራ (አልጄሪያ) (1-1) (ናምዲ አዚኪዊ ስታዲየም)

16፡00 – ሪቨርስ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) ከ ኤኤስ ሪያል ደ ባማኮ (ማሊ) (0-0) (ሊብሬሽን ስታዲየም)

16፡00 – ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) ከ ኮት ደኦር (ሲሸልስ) (2-0) (ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም)

17፡00 – ክለብ ዴስፖርቲቮ ደ አውጉስቶ (አንጎላ) ከ ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ) (0-1) (ስታዲዮ ኖቬምበር 11)

17፡00 – ሆሮያ (ጊኒ) ከ ዩኤስ ጎርን (ሴኔጋል) (0-0) (ስታደ 28 ሴፕቴምበር)

17፡00 – ስታደ ማሊያን (ማሊ) ከ ባራክ ያንግ ኮንትሮለር (ላይቤሪያ) (0-1) (ስታደ ማዲቦ ኬይታ)

Leave a Reply