ዝውውር | አብዱልሀኪም ሱልጣን ወደ ጅማ አባ ቡና አምርቷል

ጅማ አባ ቡና የኢትዮ ኤሌክትሪኩ አማካይ አብዱልሀኪም ሱልጣንን በውሰት ውል አስፈርሟል፡፡ ዘንድሮ ከኤሌክትሪክ ጋር ያለው ውል የሚያበቃው አብዱልሀኪም እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ በጅማ አባ ቡና ይቆያል፡፡

በ2007 ክረምት በብሄራዊ ሊጉ ማጠቃለያ ባሳየው ብቃት ኢትዮ ኤሌክትሪክን የተቀላቀለው አብዱልሀኪም በቀዮቹ ቤት የመጫወት እድል አምብዛም ማግኘት ሳይችል ቀርቷል፡፡

ጅማ አባ ቡና ቡድኑን በሁለተኛው ዙር ተፎካካሪ ለማድረግ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾችን ከአዳማ በውሰት ውል ለማግኘት ድርድር ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡  የዩጋንዳ ዜግነት ላላቸው ሁለት ተጫዋቾች የሙከራ እድል ሰጥቶም አጥጋቢ እንቅስቃሴ ባለማሳየታቸው ሸኝቷቸዋል፡፡

1 Comment

  1. ጂማ አባ ቡና ድምፁን አጥፍቶ እየተጠናከረ ነዉ ያስፈራል

Leave a Reply