​ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሳይ ከበደን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል

ባለፈው ሳምንት አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማርያምን ያሰናበተው ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ አዲስ አሰልጣኝ ከመሾም ይልቅ በምክትል አሰልጣኙ ሲሳይ ከበደ እየተመራ ለመቆየት ወስኗል፡፡ ከ20 አመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ ግርማ ፀጋዬ ደግሞ የሲሳይ ከበደ ረዳት ሆነው ተሹመዋል፡፡

በደረጃ ሰንጠረዡ 15ኛ ላይ ተቀምጦ አንደኛውን ዙር ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰልጣኝ ሲሳይን እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ እንዲያሰለጥኑ ኃላፊነት የሰጠ ሲሆን የቡድኑን ውጤት ካሻሻሉ ቋሚ ኮንትራት ሊቀርብላቸው እንደሚችል ተሰምቷል፡፡

አሰልጣኝ ሲሳይ ክለቡ ባሉበት ክፍተቶች ላይ በተለይም በተከላካይ እና አማካይ ላይ የተለየ ትኩረት አድርገው ተጨዋቾችን በውሰትም ሆነ በፊርማ ለማስመጣት እየተናቀሳቀሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply